የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከነሀሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኘውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና ፍየሎች የሚገኝው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የተረፈ ምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከነሀሴ 01 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2018ዓ.ም ለሚያመርተው በየእለቱ ከሚታረዱ ከዳልጋ ከብት የሚገኝውን እርጥብ ቆዳና ከበጎች እና የፍየሎች የሚገኝው እርጥብ ሌጦ፣ የስጋና አጥንት መኖ፣ የዳልጋ ከብት ቀንድ እና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-

  • በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ አለበት፡፡
  • የጨረታ ማስከበሪያን በተመለከተ ለዳልጋ ከብት ቆዳ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሦስት የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና በወር ውስጥ ለሚገኝው የበግና ፍየል ሌጦ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሲሆን የዳልጋ ከብት ቆዳ ጨረታ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ለ10 ቀናት ብር 4,000,000.00 (አራት ሚሊዮን ብር) እና የበግና ፍየል ሌጦ ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች የቅድመ ክፍያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ለስጋና አጥንት መኖ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለዳልጋ ከብት ቀንድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) እና ለተነጠረ ሞራ ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ለዳልጋ ከብት ቀንድ ምርቱን በሳምንት ሁለት ቀን እንዲሁም ለስጋና አጥንት መኖ ምርቱ በሚመረትበት በሳምንት  ሦስት ቀን (ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ሐሙስ) እና ለተነጠረ ሞራ ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  • ምርቱን ለመግዛት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች በጨረታ መመሪያ ላይ በተገለፀው መሰረት ይሆናል፡፡
  • አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል፡፡
  • ከቆዳና ሌጦ ውጪ ላሉት ምርቶች የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል፡፡
  • ጨረታው ለዳልጋ ከብት ቆዳ እና ለበጎች እና ፍየሎች እርጥብ ሌጦ ሀምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ለተነጠረ ሞራ ሀምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ለስጋና አጥንት መኖ ሀምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እና ለዳልጋ ከብት ቀንድ ሀምሌ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት!!!


Tender details

  • Deadline: 2026-08-04
  • Publishing entity: Addis Ababa Abattoirs Enterprise
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ከቆዳና ሌጦ ውጪ ላሉት ምርቶች
  • Published: Jul 21, 2026
  • Posted at: 2026-07-21T08:19:17+00:00

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders