በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል 2019 ዓ.ም በጀት አመት ለሆስፒታሉ የሚውሉ የታካሚዎች የበሰለ ምግብ አቅርቦት እንዲሁም የሰራተኛ ክበብ (ካፌ) አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
ለ2ኛ ጊዜ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል 2019 ዓ.ም በጀት አመት ለሆስፒታሉ የሚውሉ
1ኛ የታካሚዎች የበሰለ ምግብ አቅርቦት
2ኛ ሰራተኛ ክበብ (ካፌ) አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ ፍቃደኛ የሆነ
1. በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ለስራው የምዝገባየምስክር ወረቀት ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ TIN/ ያላቸው።
2. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 50 በግዥ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሃደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ.ብር 300/ሶስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብክመ ክሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስራ ስድስተኛው/16ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ግዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው በአስራ ስድስተኛ ቀን 4፡02 ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈል የመክፈቻ እለቱ የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ በተራ ቁ1 እና ቁ2 ለተገለፀ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ ትእዛዝ CPO ማስያዝ አለባቸው።
6. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ግዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ እስከ 10% “ማስያዝ ይኖርበታል።
7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይንም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. የመስሪያ ቦታ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል ይሆናል።
9. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ (ሎት) የምንወስድ መሆኑን እንገልፃለን።
10. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 0972847872 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
በአማራ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የከሚሴ ጠቅላላ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-08-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛ ቀን 4፡02
- Bid opening: 2026-08-05 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛ ቀን 4፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Kemise General Hospital
- Bid bond: 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published: Jul 21, 2026
- Posted at: 2026-07-21T08:25:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.