በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት 1ኛ ዙር የግልጽ

ጨረታ ማስታወቂያ

1ኛ. አላቂ እና ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፤ የጽዳት እቃዎች፤የደንብ ልብስ፤ የጓሮ አትክልት ዘር ግዥ፤ የመኪና ዲኮር እቃዎች ግዥ

2ኛ. የአመት ውል፡- የቢሮ ማሽን ጥገና (ኮምፒዩተር፤ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ሰርቪስና ጥገና)፤የህዝብና የእቃ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት፤የቢሮ እድሳትና ጥገና ፤የህትመት ስራ፤የዲጄና ዲኮር አቅርቦት፤የቢሮ ፈርኒቸሮች ጥገና፤የጉልበት ስራ አገልግሎት፤የ90 ቀን ዶሮ እና መኖ ግዥ ፤ የዶሮ ኬጅ ግዥ፤የሰራተኛ ካፌ አገልግሎትና መስተንግዶ አቅርቦት፤ጀነሬተር ሰርቪስ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን የ2018 ዓ.ም የመንግስት ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።
  2. የቫት ተመዝጋቢና ህጋዊ የአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በየሎቱ በመክፈል የጨረታ ሰነድ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 ውስጥ የተገለጹትን እቃዎች ዝርዝር ዋጋቸውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በቂ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚህ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር
    • ሎት 1. የደንብ ልብስ 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ )በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
    • ሎት 2. የፅዳት እቃዎች 20,000.00(ሀያ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
    • ሎት 3. አላቂ የቢሮ እቃዎች 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
    • ሎት 4. ቋሚ የቢሮ እቃዎች 35,000.00 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
    • ሎት 5. ህትመት ስራ ፤የሰራተኛ ካፌ አገልግሎትና መስተንግዶ፤ዲጄና ዲኮር አቅርቦት ፤ የሰውና እቃ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
    • ሎት 6. ጀነሬተር ሰርቪና ጥገና፤የቢሮ ፈርኒቸር ጥገናዎች፤የቢሮ እድሳትና ጥገና፤የቢሮ ማሽን ጥገናና ሰርቪስ፤የጉልበት ስራ አገልግሎት ብር 4,000.00 (አራት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
    • ሎት 7. የጓሮ አትክልት ዘር ግዥ ፤የዶሮ ኬጅ ግዥ፤የ90 ቀን ዶሮ እና መኖ ግዥ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና የማስገባት ግዴታ አለባቸው።
  7. አሸናፊ ድርጅቶች በናሙናው በስፔስፊኬሽኑ/ መሰረት ደረጃውን የጠበቀ እቃ የማስገባት ግዴታ አለባቸው።
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያኑ ቀን 4፡30 በፋ/ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
  9. መቅረብ ያለባቸው መረጃዎች፤- ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል ሁለቱም ኦሪጅናልና ኮፒ ሲሆን ለየብቻቸው መታሸግ አለባቸው። ነገር ግን ጨረታው ሲከፈት የሚከፈተው ኮፒው በመሆኑ ሲፒኦ (CPO) እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች በሙሉ ኮፒው ውስጥ መደረግ አለባቸው፡፡በሁሉም ኤንቨሎፕ ላይ የደርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት።
  10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ዋጋ ድምር 10% የውል ማስከበሪያ ከውል በፊት ማስያዝ አለባቸው ፡፡የእያንዳዱ እቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ (ቫትን ጨምሮ) መቅረብ አለበት ይንን ያላደረጉ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ።
  11. ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄዎች ወይንም መረጃ ማግኘት ለሚፈልጉ ስልክ ቀጥር 0118883069 መጠቀም ይችላሉ።

አድራሻችን፡ ደ/ዘይት መንገድ ላንቻ ባቡር ፌርማታ በስተቀኝ 100 ሜትር ገባ ብሎ ቂርቆስ

ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

ማሳሰቢያ፡- ለሰራተኛ ካፌ አገልግሎት አስተዳደሩ የውሃ፣የመብራት እና የኪራይ አገልግሎት ክፍያ እራሱ ይሸፍናል።

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በቂርቆስ ክፈለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-01
  • Publishing entity: Kirkos Sub City Woreda 4 Administration Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published: Jul 21, 2026
  • Posted at: 2026-07-21T08:27:17+00:00

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders