የቤቱ ስፋት 483 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ ገነት ብርሃኑ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ደረጀ ካሳሁን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/153243 በ27/05/2016 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/17708 በ24/06/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 022 የቤቱ ስፋት 483 ካ/ሜ የካርታ ቁጥር ቦሌ 8/10/6/8/3195/00 የሆነ ቤት እና ይዞታ ቀድሞ በሟች ወ/ሮ ፋንታዬ ገበየሁ ስም አሁን ግን ይዞታ መለያ ቁጥር ቦሌ4/6/5/5/3195/42283/01 የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 22,867,259 (ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 22, 2026
- Posted at: 2026-07-22T08:01:24.000Z
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.