የተለያዩ ቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍባለመብት አቶ ናትናኤል አብርሃም እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ሃና ሩሶም መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.299412 በቀን 26/6/2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ እና በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.321201 በቀን 5/3/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት

1ኛ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ኤ.ኤም.ቲ ኢንፖርተር ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ላይ 14ኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ በዲዛይን የተለየ የቤት ቁጥር B/14/04 ተ/ቁ የተሰራ የወለሉ ስፋት 135.9 ካ/ሜ በንጽጽር የሚደርሰው 18.25ካ/ሜ በጠቅላላ ድርሻ 154.15ካ/ሜ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 11,116,348.20 (አስራ አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ አርባ ስምንት ከ20/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛ በጊፍት ሪል ስቴት ኃ /የተ/የግ/ማ ላይ በየካ ክ/ከተማ ቀበሌ 03 በአዲሱ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሚገኝ ባለ 45 አባወራ G+10 አፓርትመንት በሳይት ቁጥር 3 የምድር ወለል ላይ የሚገኝ ሱቅ ስፋቱ 49.1 ካ/ሜ የንግድ ሱቅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,428,614 ( አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ አስራ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.0 ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሽጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌደራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 22, 2026
  • Posted at: 2026-07-22T08:05:15.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders