Stationery and office consumables

ኬር ህጻናት እና ቤተሰብ ለሆኑ ተማሪዎች ፕላስቲክ ሽፋን ሆነው የተለበዱ ሲናር ላየን ደብተሮችን እና ሌሎች እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ኬር ህጻናት እና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ለ2019 ዓ.ም/ የትምህርት ዘመን በድርጅቱ ታቃፊ ለሆኑ ተማሪዎች ፕላስቲክ ሽፋን ሆነው የተለበዱ ሲናር ላየን ደብተሮችን፦

  • 1ኛ, ባለ 50 ቅጠል ባለ መስመር፤
  • 2ኛ, ስኩዌር ባለ 50 ቅጠል ደብተሮችን፤
  • 3ኛ ኬኒያ ቢክ እና ቡና እስክሪብቶዎችን፣
  • 4ኛ, HB እርሳሶችን በየክፍል ደረጃቸው የሚያስፈልጋቸውን መጠን መግዛት ይፈልጋል

በመሆኑም፡-

  1. ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ተመዝጋቢ ሆነው በዘርፉ የታደሰ የስራ ፈቃድ ያላቸው እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 / አምስት ሺህ ብር/ በሲፒኦ በድርጅታችን ስም ማስያዝ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 5 በ 200 ብር በመግዛት ከላይ በቅደም ተከተል የተጠቀሱትን 4 አይነት የግዢ ዝርዝሮችን በድርጅታቸው ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ላይ የእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እስከነ ቫቱ በማስቀመጥ በሰም በታሸገ ኤነቨሎፕ የተጠየቁትን ሰነዶች በማሸግ ቡኢ ከተማ በሚገኘው የኬር ህጻናት እና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ድርጅት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ህትመት ገጽ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ተገኝተው ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
  4. ተጫራቾች በተጨማሪም የጨረታውን ሰነድ ሲያቀርቡ ከሚያቀርቡት ከላይ ከተገለጹት ደብተሮች፤ እስኪርብቶዎች እና እርሳሶች ለናሙና የድርጅታቸውን ማህተም በማሳረፍ በኤንቨሎፕ አሽገው ቡኢ ከተማ በሚገኘው የኬር ህጻናት እና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ድርጅት ጽ/ቤት የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት የመጨረሻው ሰባተኛ የስራ ቀን ላይ ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡኢ ከተማ የኬር ህጻናት እና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ድርጅት ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
  6. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር

046-883-0266/ 0350/0023

(የኬር ህጻናት እና ቤተሰብ ስኢትዮጵያ ድርጅት)

ጠይቆ መረዳት ይቻላል።

አድራሻ ፡-

  • የኬር ህጻናት እና ቤተሰብ ለኢትዮጵያ ድርጅት፡- በማዕከላዊ ኢ/ያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ቡኢ ከተማ ወደ አሽገዴ በሚወስደው መንገድ ከዋናው አስፓልት መንገድ 200 ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
  • ቡኢ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምህራብ አቅጣጫ ከአለምገና ወደ ቡታጅራ ከተማ በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ ከተማ በ103 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

Tender details

  • Deadline: 2026-07-29
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት የመጨረሻው ሰባተኛ የስራ ቀን ላይ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-29 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት የመጨረሻው ሰባተኛ የስራ ቀን ላይ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: ኬር ህጻናት እና ቤተሰብ
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Reporter (Jul 22, 2026)
  • Posted at: 2026-07-22T08:34:02.000Z
← Back to all tenders