ለሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ቀለብ እህል፣ ጥራጥሬ እና ሸቀጣ ሸቀጥ ከነሀሴ 1/2018 ዓ.ም እስከ ሕዳር 30/2019 ዓ.ም. ለ120 ቀናት እና የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያና የስልጠና ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

ለሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም በስሩ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ቀለብ እህል ፤ጥራጥሬ እና ሸቀጣ ሸቀጥ ከነሀሴ 1/2018 ዓ.ም እስከ ሕዳር 30/2019 ዓ.ም ለ120 ቀናት እና የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያና የስልጠና ዕቃዎች ከሚያቀርቡ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች አቅራቢ ነጋዴዎችና ማህበራት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች፡

1ኛ/ በየዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ

2ኛ/ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3ኛ/ የጨረው ተወዳዳሪዎች ለእህል ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 50000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ እና ለሸቀጣ ሸቀጥና ለጥራጥሬ ጨረታ ማስከበርያ 20000/ሃያ ሽህ ብር በጥሬ በባንክ የተረጋገጠ ሲፕኦ በማስያዝ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ሰነድን መግዛት የሚችል፣

4ኛ/ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በስም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ያለውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5ኛ/ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል።

6ኛ/ ጨረታ የሚከፈትበት ቀን የመንግስት ሥራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ይከፈታል።

7ኛ, የጨረታው አሽናፍ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በራሱ ወጭ ለማሻ ማ/ተቋም ማስረከብ የሚችል

8ኛ/ ተጫራቾች አሁን ባቀረቡት ዋጋ ለ4 ተከታታይ ወር ማቅረብ የሚችል ሲሆን በመሀሉ የድርድር ጥያቄ ተቀባይነት የለውም

9ኛ ተጫራቾች ህጋዊ መጋዘን ስለመኖራቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣

10ኛ ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል የመስረዝ መብቱ በህ የተጠበቀ ነው።

በሸካ ዞን ማሻ ማረሚያ ተቋም


Tender details

  • Deadline: 2026-08-06
  • Publishing entity: Sheka Zone Masha Correctional Facility
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jul 22, 2026
  • Posted at: 2026-07-22T09:48:06.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders