በደቡብ ኢት/ ክልላዊ መንግስት ባስከቶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በዞናችን የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ/የማይሰራ/ መኪናዎች፣ ጀነሬተሮችና ሞተር ሳይክሎች በሚገኙበት ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢት/ ክልላዊ መንግስት ባስከቶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በዞናችን የሚገኙ የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ /የማይሰራ/ መኪናዎች፣ ጀነሬተሮችና ሞተር ሳይክሎች በሚገኙበት ቦታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች፦

1. ተሽከርካሪዎች /ጀነሬተሮች እና ሞተር ሳይክሎች የሚገኙበት አድረሻ ባስከቶ ዞን ላስካ ከተማ ዞን አሰ/ር ጽ/ቤት ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ እና ላስካ ሆስፒታል ቅጥር ግብ ውስጥ ይገኛል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን ከማቅረባቸው በፊት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ቀናት በአካል በመገኘት ከላይ በኩል በተገለጹት አድራሻ አስቀድመው ማየት እና ሲመለከቱ ከጫረታ ሰነድ ጋር ልዩነት መኖሩን ሲያረጋግጡ ጨረታው ከመስተ እምነት የሥራ ቀናት በፊት ለፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ማሳወቅ አለባቸው። ይህን ሳያደርጉ የቀሩ ተጫራች ጨረታው ከታሸገ በኃላ ለሚቀርበው አቤቱታ መ/ቤቱ ምንም ምላሽ ለመስጠት አይገደድም።

3. ለተሽከርካሪዎች ጀነሬተሮች እና ሞተር ሳይክሎች ጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድረጅት መሳተፍ ይችላል።

4. ተጫራቾች የሚገዙትን የተሽከሪካር /ጀነሬተሮች/ እና ሞተር ሳይክል በሚገዙበት የጨረታ መግዣ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በደቡብ ኢ/ያ ክ/መ/ ባስከቶ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ስም በማቅረብ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላሉ። ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቦኃላ ከውድድሩ ቢወጡ የጨረታው ማስከበሪያው ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

5. የአሽናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተገለጸበት ጀምሮ አምስት ከሥራ ቀን ቦኃላ ጨረታውን ላላሸነፈ ተጫራቾች ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ተመላሽ ይደረጋል።

6. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 09 የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

7. ማንኛውም ተጫራቾች በዋጋ ማቅረብያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሀዝና በፊደል በመጻፊ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለበት ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም።

8. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን ተሽከርካሪ /ማሽነሪ ንብረት ዋጋ በአንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ CPO) የተጨመረበት ሁለት በፖስታ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/11/2018 ዓ.ም ዕለት ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖረባቸዋል በዕለቱ 8፡30 ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ይሆናል።

9. ተጫራቾች ዘግይቶ የደረሰ ተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የለውም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን ሂደቱን አያስተጓጉልም።

10. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉት ተሽከርካሪና ማሽነሪ ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ በመክፈል ማንሳት አለባቸው በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ያስያዙት CPO) ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሜ ጨረታ ይወጣል።

11. መ/ቤቱ የጨረታ ሰነዱ መስተካከል አለበት ብሎ ሲያምን ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ማስተካከል የሚችል ሲሆን ይህንንም ለሁሉም ተጫራቾች በማስታወቂያ ሰልዳ ላይ ግልጽ ያደርጋል።

12. መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0916720827 እና 0913988604 ይደውሉ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባስኬቶ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid opening: 2026-08-03 14:30
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: SNNPRS Basketo Special Woreda FEDB
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: Jul 23, 2026
  • Posted at: 2026-07-23T07:51:42.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders