የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 22/11/2018 እና 25/11/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች፡-
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ ዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 22/11/2018 እና 25/11/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።
3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ/ቁ |
የጨረታ ቦታ
|
የጨረታው አይነት
|
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች
|
የዕቃዎች መመልክቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝግያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ቃሊቲ ጉ/ቅጽ/ ቤት
|
ግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ |
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ ፣ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች፣ ጠፍጣፋብረት፣ ላሜራ፣ የወዳደቁ ብረቶችና ፕላስቲኮችእና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች
|
ለግልጽና ለሐራጅ 22/11/2018 እና 25/11/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45
|
ለግልጽ ጨረታ 22/11/2018 እና 25/11/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 22/11/2018 እና 25/11/2018 ዓ/ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል።
|
5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች በጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-01
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-08-01 11:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Oromia
- Publishing entity: Awash Custom Commission Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published: Jul 23, 2026
- Posted at: 2026-07-23T07:51:45.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.