Stationery and office consumables
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት /አገና/ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች፣ የተለያዩ ፈርኒቸሮች እና የተለያዩ ሞተሮች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ማለትም፡-
- ሎት 1 የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት2 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች
- ሎት3 የተለያዩ ፈርኒቸሮች
- ሎት4 የተለያዩ ሞተሮች
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑ ግብር በመክፈል ፍቃድ ያደሳችሁ እና ፍቃዳቹ ኦንላይን የተመዘገባቹ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(ቲን) ማቅረብ የሚችሉ።
- በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተወዳዳሪዎች ለወረዳችን 7.50% ገቢ የምታደርጉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ገንዘብ ለሎት1. 20,000 (ሀያ ሺህ)፣ ለሎት2 20,000(ሀያ ሺህ) ለሎት3 20,000(ሀያ ሺህ) እና ለሎት4 20,000 (ሀያ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠለት ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በእዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸው እቃዎች እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አጠቃላይ በአንድ ጊዜ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱን ሎት የጨረታው ዝርዝር የያዘ ዶክመንት ለመግዛት የሚያስችል የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00ሰዓት ድረስ ሰነዳቸው ፋይናንስ ጽ/ቤት ግ/ከ/ን/አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀ ቀን ጀምሮ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታው ማሸነፋቸውን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበርያ አሰርቶ ውል ካልፈፀሙ መስርያ ቤቱ የጨረታ ማስከበርያውን የመውረስ መብት አለው።
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማለትም ቅዳሜና እሁድ እዲሁም የበዓል ቀናት ጨምሮ አየር ላይ ይውላል:: ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በ15 ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገርግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የተጫረቱባቸው እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
ማሳሰቢያ፡- ሰነዱ ማግኘት የሚቻለው ተወዳዳሪው በአካል ወይንም ህጋዊ ለሆነ አካል ብቻ ነው።
ወረዳው በጉራጌ ዞን ከወልቂጤ ከተማ 42 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ 197 ኪ.ሜ ላይ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 09-23-13 37-39 እና 09-23-51 95-14
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን
እዣ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት /አገና/
Tender details
- Deadline: 2026-08-06
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት በ15 ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-06 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት በ15 ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Gurage Zone Ezja Wereda FEDB
- Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Jul 23, 2026)
- Posted at: 2026-07-23T08:31:53.000Z