የሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና፣ የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያቁ-01/2019

የሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት 2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ፈርኒቸር፣
  • የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች፣
  • የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና
  • የመኪና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃደቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ( tax Payer Registration No.) ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች እና የመኪና የሞቶር ሳይክል ጎማዎችን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 550 (አምስት መቶ ሃምሳ ብር) እና ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎችና የጽዳት እቃዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር (አራት መቶ ብር) ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000041404004 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ ንብረት አስተዳደር፣ ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው መከፈላቸው እና ጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ መቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙለት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቢሮ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ እና የመኪና የሞቶር ሳይክል ጎማዎችን ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 45,000.00 (አርባ አምስት ሺህ ብር)፤ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር)፤ ለጽዳት እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ) በአቅራብያችሁ የሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዝ (CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ በቦቆጅ ከተማ ውስጥ በሚገኘው ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
  7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማረጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0962278710,0910776822 ይጠይቁ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአርሲዞን የሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-10 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: Jul 23, 2026
  • Posted at: 2026-07-23T08:36:57.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders