በምዕራብ ወለጋ ዞን የሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳው መደበኛ በጀትና ለወረዳው የተሰጠ የተለያዩ ፈንድ እና የመሳሰሉት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ ወለጋ ዞን የሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በወረዳው መደበኛ በጀትና ለወረዳው የተሰጠ የተለያዩ ፈንድ እና የመሳሰሉት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች

1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች

2. አላቂ የጽዳት መገልገያዎች

3. ከአንድ ዓመት በላይ የሚያገለግሉ የቢሮ መገልገያ መሣሪያዎች

4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

5. የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸሮች

6. የግንባታ ዕቃዎች

7. የመኪና ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማ

8. የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ

1. ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች የማይመለስ የጫረታ ሰነድ ብር 1000 (አንድ ሺህ )ብር ብቻ በመክፈል ይህ ጫረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤ/ት በቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ተጨማሪ የእሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ መቻል አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚሆን ከላይ የተገለጹት ዕቃዎች፤ ለተራ ቁጥር 1፤ 2 እና 3 ብር 40000 ለተራ ቁጥር 4 ብር 40000 ለተራ ቁጥር 5 ብር 40000 ቁጥር 6 ብር 30000 ለተራ ቁጥር 7 ብር 30000 ለተራ ቁጥር 8 ብር 30000 በእጅ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለበት።

3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ቴክኒከል ዶክመንት ዋናውን በአንድ ፖስታ ኮፒውን በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን በአንድ ፖስታ በማሸግ ፋይናንሻል ዶክሜንት ዋናውን በአንድ ፖስታ ኮፒውን በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን በአንድ ፖስታ በሰም በማሸግ ኤንቨሎፕ ላይ የተወዳዳሪውን ማንነት የሚገልጽ ስምና ፊርማ በመጻፍ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሃያ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሐሩ ወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

4. የጨረታው የምዝገባ ጊዜ ከ17/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21/12/2018 ዓ.ም የሥራ ቀን ሲሆን በ21/12/2018 ዓ.ም በ6፡00 ሰዓት ተዘግተው በዚህ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በከፊል ባይገኝም ጨረታውን አያሰናክልም።

5. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆኖ ሲቀርቡ ዕቃዎቹን በራሳቸው ወጭ እስከ ሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

7 አሸናፊ ተጫራቾች ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. የወረዳ ገንዘብ /ጽ/ቤት ጨረታውን ለመገምገም የሚጠቅምባቸውን መስፈርቶች ዕቃዎቹ ወረዳው ባስቀመጠው እስፔስፊኬሽን ለዕቃዎቹ የተሰጠ ዋስትና ለዕቃዎቹ ጥራት አነስተኛ ዋጋ እና አጠቃሎ የማቅረብ ጊዜ ግምት ውስጥ ይገባል።

9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

10.ተጫራቾች አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች እስክብሪቶ፣ የኮምፒውተር ቀለም፣ ወረቀት፣ ፍሉድ፣ ውሁ፣ አጀንዳ፣ ቦርሣ እናመዝገብ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

ተጨማሪ ማብራሪያ፡-
በስልክ ቁጥር 0935898000/0976549827
/0957895728/0905067099
በምዕራብ ወለጋ ዞን የሐሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-08-27 14:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Haru District Finance & Economic Dev't Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published: Jul 24, 2026
  • Posted at: 2026-07-24T07:31:49.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders