የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር 4ኛ ችሎት ስፋቱ 255 ካ/ሜ የሆነ ቤት የጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል
Description
የመ/ቁ 102169
ቀን 19/10/2018 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ ኢብራሂም ኡስማን አሊ እና በፍ ባለዕዳ አቶ እወድ ኡስማን አሊ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 100389 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ቀበሌ 08 ክልል ውስጥ የሚገኝ በካርታ ቁጥር 3833 በቤት ቁጥር 4056 የሆነና ስፋቱ 255 ካ/ሜ የሆኖ በሟች ወ/ሮ ፋጡማ ፋራህ የተመዘገበ ቤት በመነሻ ግምት ብር 3,065,661 /ሶስት ሚሊዮን ስልሳ አምስት ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ አንድ ብር/ በሆነ ዋጋ በሃራጅ ሽያጭ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል። ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡10 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡15 እስክ 5፡00 ባለው ጊዜ ይከናወናል። በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች ለሃራጅ ጨረታው ከመዝገቡ በፊት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ቀድሞ በCPO በባንክ አስይዘው እንዲመዘገቡ ታዟል
የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በCPO ወይም በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው። ቀሪውን 3/4ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል።
የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት ፍትሐብሔር 4ኛ ችሎት
Tender details
- Deadline: 2026-10-17
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-10-17 11:00
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 15, 2026
- Posted at: 2026-07-24T08:04:56.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.