የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ በጀት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ በጀት

  • ሎት 1. እስቴሽነሪ እና የፅዳት ዕቃዎች
  • በሎት 2. ፈርኒቸር ዕቃዎችን እና
  • ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት -

1- ተጫራቾች በ2019 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (ክሊራንስ ያላቸው) በክልል ወይም በፌዴራል በክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም መምሪያ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው እና ማረጋገጫና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ / BlD Security/ 20000/ ሃያ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ መዘዣ (CPO ወይም Unconditional bank guarantee ማቅረብ ይኖርበታል።

2. በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.ዕታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ብር በመክፈል ደረሰኛቸውን በመያዝ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security)፣ ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ - ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 አስከ 5:30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት  አያግደውም።

5. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

6. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

7. የቀረበው ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒው የማይታይ እና የማይነበብ ከሆነ እንዲሁም የሚያጠራጥር ሁኔታ ቢገኝ  ኦርጅናሉን የማቅረብ ግዴታ አለበት።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-08
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 5፡30
  • Bid opening: 2026-08-08 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Yirga Alem City FEDB
  • Bid bond: 20,000 (ሀያ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jul 24, 2026
  • Posted at: 2026-07-24T08:14:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders