Stationery and office consumables

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ስር የሚገኘው የወረዳ 11 ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችና ስራዎች በ1ኛ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ስር የሚገኘው የወረዳ 11 ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎችና ስራዎች በ1ኛ ዙር ን/ሰ/ወ11/001/2019 ዓ.ም ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

እነሱም፡ የደንብ ልብስ፤ አላቂ የጽህፈት እቃዎች፤ የጥገና እቃዎች፤ ቋሚ እቃዎች፤ የጥገና ስራ፤ የህትመት ስራ፤ ሻይ ቡና፤ የኮምፒዩተር ጥገና፤ የፕሪንተር ጥገና፤ ፎቶ ኮፒ ጥገና እና የጽዳት እቃ፤ መግዛት ይፈልጋል።

ሆኖም ተጫራቾች እቃው በእስቶር ውስጥ ስለመኖሩ ወይም የቴክኒክ ባለሙያዎች መተው ማየት ሲፈልጉ እንደሚያቀርቡ ማረጋገጫ ደብዳቤ መስጠት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ።

1. ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘመኑ ግብር የተከፈለበት እና የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ፣

2. በመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ላይ የተመዘገቡ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚችል ድብዳቤ ማቅረብ የሚችል።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ቫት/ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እንዲሁም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ከአደራጃችው አካል ድብዳቤ እና ደብዳቤው ሼድ እንዳላቸው የሚገልጽ መሆኑን አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት ተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ውስጥ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 ዘወትር በስራ ሰዓት 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይኖርባችኋል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዝርዝርና ዋጋ እና መለያ ቁጥር ከላይ ከተጠቀሰው ተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማህተምና ፊርማ በማኖር ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ አራተኛ ፎቅ በግዥ ቡድን መሪ ቢሮ ውስጥ ባለው በታሸገ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. በመክፈቻ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታውን ሳጥን መክፈቻ ስነ- ስርዓት አያስቀርም።

7. ፋይናንሻል እና እንዲሁም ቴክኒካል ኦርጅናል ብሎ በመለየት በአንድ ፖስታ በማሸግ ፊርማ እና ማህተም በማደረግ ማስገባት አለባቸው።

8. የጨረታ ማስከበሪያ የግዥውን 1(80,000) (ሰማኒያ ሺህ ብር ብቻ)

9. የጨረታ ሳጥን በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በጤና ጣቢያው ይከፈታል።

10. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ መ/ቤቱ ናሙና ራሱ አቅርቦ ዕጩ ተወዳደሪዎች ለእይታ አስቀርቦ በናሙና መሰረት እንዲያቀርቡ የሚያደርጋቸው ግዥዎች መኖራቸው እንዲታወቅ፡፡ የሚቅረቡ ናሙናዎች ብዛት በዋጋ ሰነድ ላይ ይመለከቱ የሚቀረቡበት ጊዜ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ሲሆን የሚቀርቡት ክፍል ራሱ በተዘጋጀው ክፍል ነው:: ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙና በሚመረመርበት ወቅት በእቃው ባህሪ ምክንያት ቢበላሽ ቢጠፋ ካሳ አይከፈለም:: ውጤት ከተገለጸበት ቀን አነሰቶ በ6 ወር ውስጥ ካልወሰዱ በውርስ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. መደበኛ የጨረታ ሰነድ (SBD) ከተቋሙ የተወሰዱትን አንብቦ እና የተሞላ አድርጎ ሙሉ በሙሉ የጨረታ ሰነዱን መመለስ /ማስገባት/ ይኖርባቸዋል።

የመስሪያ ቤቱ አድራሻ

ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 11 ጤና ጣቢያ ልዩ ስም ሀና ማርያም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት።

ለበለጠ መረጃ : የስልክ ቁጥር፡- 011-47-119-74

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የወረዳ 11 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-06 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአስረኛው በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nifas Silk Lafto Sub City Woreda 11 Health Post
  • Buyer address: በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ  11 ጤና ጣቢያ ልዩ ስም ሀና ማሪያም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት
  • Bid bond: 80,000.00 ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Jul 25, 2026)
  • Posted at: 2026-07-25T08:19:30.000Z
← Back to all tenders