Office and commercial space rental

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ጥቅል ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር ጥቅል ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ የሚቾች እንድትወዳደሩ እያሳወቅን።

      የእቃው አይነት                 የጨረታ ማስረከቢያ በኢትዮ ብር

  • ሎት 1 የእስቴሽነሪ እቃዎች….25000 ብር  
  • ሎት 2 የፅዳት እቃዎች…25000 ብር   
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ ዕቃዎች…..30000 ብር   
  • ሎት 4 የህትመት አገልግሎቶች….10000 ብር   
  • ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎቶች…..5000 ብር   
  • ሎት 6 የትራንስፖርት አገልግሎት…5000 ብር   
  • ሎት 7 የመስተንግዶ አገልግሎቶች….5000 ብር   
  • ሎት 8 የሰራተኛ ካፍቴሪያ አገልግሎቶች…1000 ብር   
  • ሎት 9 የተለያዩ ኪራይ አገልግሎቶች…..5000 ብር   

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው።

3. የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል።

4. ለሚያቀርቡት እቃ የጥራት ደረጃውን የሚገልጽ ስልጣን ከተሰጠው አካል የተረጋገጠ ማስረጃ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል።

5. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

6. ተጫራቾች ከዚህ በታች ለተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።

7. የጨረታ ሰኦዱን ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመከፈል ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 305 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሎች 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 305 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9, ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በሚቀጥለው ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10 ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስረከብ 10% ማስያዝ አለባቸው።

11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ለማይቀርብባቸው ቋሚ ኢቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኪሽን መሰረት ወይንም በፎቶ ማቅረብ አለባቸው።

12. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ድረሰ ማቅረብ ይኖርበታል።

13. መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ቢፈጠር ከፊት ለፊት ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የተሞላው ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።

16. የጨረታ ሰነዱ አንዱ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች ሊረዱት የሚገባ ሲሆን ኦርጅናል የጨረታ ሰነዱ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማስገባት መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በጨረታ ሰነዱ ያልተካተቱ ችግሮች ቢያጋጥሙ በግዥ መመሪያ መሰረት የሚዳኝ ይሆናል።

17. የሚሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።

18. ጨረታውን ለመወዳደር የእቃ ጥራት እና የዋጋ ዝቅተኛነትን ግምት ውስጥ የምናስገባ ይሆናል።

19. የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት ወይንም እንቅፋት ለመፍጠር የሚሞክር ከጨረታ ውጭ ይደረጋል።

20. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ለውጥ ወይንም ማሻሻያ ማድረግ እና እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ እንዲሁም ለአንድ እቃ ለሚቀርበው ናሙና ተለዋጭ ናሙና ማቅረብ አይቻልም።

21. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ፡- ከሚያደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ፤ ምን አይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ ወይንም ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራች የተሰጠ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ፕላዛ ሆቴል 100 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በአካል በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 0118 53 89 53 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት

በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-06 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በሚቀጥለው ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Sub City Administration Woreda 04 FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Lessan (Jul 25, 2026)
  • Posted at: 2026-07-25T09:11:20.000Z
← Back to all tenders