Grains, pulses and staples
የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት በ2019 ዓ/ም ለታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውሉ ጥሬ ሰብሎችና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት በ2019 ዓ/ም ለታራሚዎች ምግብ ዝግጅት የሚውሉ ጥሬ ሰብሎችና የተለያዩ ማጣፈጫዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ እና በተወዳዳሪዎች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. ጥራት ያላቸውን የተጠየቁ ጥሬሰብሎች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የተለያዩ ማጣፈጫዎችን እና የዳቦ ዱቄት ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
3. ለምግብ ማብሰያ የሚሆን ግንድላ /ማገዶ እንጨት ማቅረብ የሚችል፤
4. ተወዳዳሪዎች የተጠየቁትን ናሙና ሙሉ በሙሉ ማቅረብ አለባቸው፤
5. የ2018 ዓ/ም ግብር አጠናቅቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታክስ ከፋይነት(TIN) (TOT)
6. ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) 50,000.00 ብር ከኦርጅናል ማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር (100) በመክፈል የግዥ ክፍል ከምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት መግዛት ይችላሉ፤
8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዓይነቶች እንደዚሁም የድርጅቱን ስም በሚያቀርቡት ፖስታ ላይ በኦሪጅናሉና በኮፒው ላይ በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተወዳዳሪዎች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
12. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0577710193 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
14. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-13 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: West Wollega Zone Correctional Facility
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T07:00:53.000Z