Stationery and office consumables

በልደታ/ክ/ከተማ ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን እና ስራዎችን በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 01

በልደታ/ክ/ከተማ ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ጥቅል ግዢ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ህጋዊ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መሳተፍ ይችላሉ።

  • ሎት 1 ቋሚ የቢሮ እቃ፣
  • ሎት2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
  • ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 4 የደንብ ልብስ እና የብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ አልባሳት፣
  • ሎት 5 የስፖርት ትጥቅና የስፖርት እቃዎች
  • ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 7 የህንጻ መሳሪያ እቃዎች፣
  • ሎት 8 የትምህርት እቃዎች
  • ሎት 9 የህክምና እቃዎች
  • ሎት 10 የዜማ መሳሪያዎችና ባህላዊ እቃዎች፣
  • ሎት 11 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣
  • ሎት 12 ህትመት፣
  • ሎት 13 ውሃ ለስላሳና ደረቅ ምግቦች
  • ሎት 14 ህንጻ እድሳት፣
  • ሎት 15 ላብራቶሪ እቃዎች
  • ሎት 16 አጋዥ መጻህፍት

1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የእቃ አቅራቢ ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ከመንግስት ግዢ ኤጀንሲ የተሰጠ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

2. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃቸው ባለስልጣን ደብዳቤ ለሚያመጡት የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድና ሶስት ፐርሰንት ቅናሽ የሚደረግላቸው እራሳቸው ላመረቱት እቃና ቫልዩ አድ ላደረጉት እቃ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎቱ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዝርዝር ዋጋ እና መለያ ቁጥር በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ማስረጃውን ከቫት ጋር እና ቫትን ሳያካትት ግልፅ በሆነ መንገድ ዋጋው ተለይቶ መቅረብ አለባቸው፡፡

6. የመወዳደሪያ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ለዋጋ መስጫ በተዘጋጀ ቦታ ያለቫት እና ከቫት ተለይተው መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀናት በፊት ኦርጂናልና ደረጃውን የጠበቁ ናሙና በት/ቤቱ ንብረትከፍል ገቢማድረግ ይኖርባቸዋል።

8. የጨረታ ሳጥን ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በ11ኛው ቀን በ3፡00 ታሽጎ በእለቱ በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት የስራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ይሆናል፡፡ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት  የጨረታ ሳጥን መክፈቻ ስነ-ስርዓቱን አያጓትትም፡፡

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈፃሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. የዘገየ ጨረታ በጨረታ መክፈቻ ቀን ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

11. ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ት/ቤቱ እስከ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ሎት

ብር

ሎት 1

5000.00

ሎት 2

3000.00

ሎት 3

3000.00

ሎት 4

4000.00

ሎት 5

3000.00

ሎት 6

4000.00

ሎት 7

3000.00

ሎት 8

3000.00

ሎት 9

3000.00

ሎት 10

3000.00

ሎት 11

3000.00

ሎት 12

3000.00

ሎት 13

3000.00

ሎት 14

3000.00

ሎት 15

3000.00

ሎት 16

3000.00

አድራሻ፡- ከሳርቤት ዝቅ ብሎ ቫቲካን ኤምባሲ ወርደው ወደ ሀረር ክሊንክ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር- 0113834219/ 0118390627

በልደታ/ክ/ከተማ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሳጥን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ3፡00
  • Bid opening: 2026-08-07 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ሳጥን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ3፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tesfa Elementary School
  • Buyer address: ከሳርቤት ወደ ቫቲካን ኢንባሲ በሚወስደው መንገድ አዲስ አበባ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ንፋስ ስልክ ላፍቶ ምድብ ችሎት ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T07:20:03.000Z
← Back to all tenders