Stationery and office consumables

የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮ መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የቂ/ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮ መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 2 ቋሚ አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን
  • ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 4 የሰራተኛ ደንብ ልብስ
  • ሎት 5 ኮምፒውተርና ፕሪንተር ጥገና
  • ሎት 6 የመስተንግዶ የካፌ አገልግሎት
  • ሎት 7 በስብስባ ወቅት የትራንስፖርት አገልግሎት
  • ሎት 8 ህትመት
  • ሎት 9 የመስተንግዶ አገልግሎት
  • ሎት 10 የዲጄ እና ዲኮር
  • ሎት 11 የዶሮ እና መኖ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ ቲን ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ፈቃድና የአገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ለተደራጁ በተወዳደሩበት ዘርፍ አምራች መሆናቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ መኖር አለበት የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው ፣ቲን ሰርተፍኬት፣ እና የዘመኑን ንግድ ፈቃድና የአገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉ መሆን አለባቸው በተጨማሪ የደረጃ ዕድገት ሰርተፍኬት፣የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር እና የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የሙያ ብቃት ሠርተፍኬት እና ከተደራጁበት የድጋፍ ደብዳቤ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ ማምጣት መቻል አለባቸው የመስተንግዶ የካፌ ቤት ኪራይ እና መብራት ውሃ ነጻ ነው።

2.የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ በእያንዳንዱ ሎት 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በቂርቆስ ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 መግዛት ይችላሉ።

3.ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ የቂርቆስ ክ/ከ/ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ 3ኛፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ቀርበው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4.ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።

5.የጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ወጪ እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች በጨረታው ስፔስፊኬሽን መሰረት ብቻ እና ናሙና የማቅረብ ግዴታ። ነው፡፡

7. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ላይ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10፡10 የሚከፈት ይሆናል፡፡

8.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9.ተጫራቾች በጨረታ አፈፃፀም ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅና መመሪያ መሰረት በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ማቅረብ ይችላሉ።

10. የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ

  • ሎት 1 (90,000)
  • ሎት 2 (45,000)
  • ሎት 3 (90,000)
  • ሎት 4 (110,000)
  • ሎት 5 (6,000)
  • ሎት 6 (43,946.40)
  • ሎት 7 (12,000)
  • ሎት 8 (9,000)
  • ሎት 9 (21,973.20)
  • ሎት 10 (6,710.88)
  • ሎት 11 (21,000)ማስያዝ አለበት

10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበራያ COP ብቻ ሊያሰራ የሚችል ሲያሰራም ለቂ/ክ/ከ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ብሎ ማሰራት ይኖርበታል፡፡ (ቼክና ጥሬ ገንዘብ፣ ቢድ ቦንድ ማስያዝ አይቻልም፡፡)

አድራሻችን፡- አጎና ሲኒማ ፊት ለፊት ከያሬድ ቤተ ክርሰቲያን ከፍ ብሎ መስቀል ፍላወር አጠገብ ወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት ህንፃ ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-18-27-59-18

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-06
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ላይ 10፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-06 16:10
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ላይ 10፡10 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kirkos Sub City Woreda 03 Administration Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T07:25:34.000Z
← Back to all tenders