Stationery and office consumables

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ/ም በጀት አመት ለአንደኛ ዙር የወጣ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ እና ውል መፈፀም ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ/ም በጀት አመት ለአንደኛ ዙር የወጣ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ እና ውል መፈፀም ይፈልጋል፤

የዚህም ጨረታ የገንዘብ ምንጭ የመንግስት ግምጃ ቤት እና የውስጥ ገቢ ነው፡፡

በዚህ መሰረት ተጫራቾች

  • ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለቸው
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉ
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ

ስለመሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከአደራጃችሁ ተቋም የአምራችነት ደብዳቤ በማምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 411 የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ ሰነዱ ውስጥ በሚገኝ የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር መሰረት ከነቫቱ ሞልተው ያስገባሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ የፅህፈት እቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 1.5%) 10000 ብር
  • ሎት 2 ቋሚ እቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 1.5 %) 51750 ብር፤
  • ሎት 3 የተለያዩ ህትመቶች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 1.5 %) 11250 ብር፤
  • ሎት 4 የፅዳት እቃዎች (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 1%) 15000 ብር፤
  • ሎት 5 የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና ስፌት (ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 1% 20000 ብር፤
  • ሎት 6 የተለያዩ የጥገና ስራዎች እና የጥገና ዕቃዎች(ለዕቃው ግዥ ከተበጀተው 1.5 %) 21750
  • ሎት 7 ለቢሮ ጥገና ስራ የሚያገለግሉ እቃዎች 2%) 4000
  • ሎት 8 የካፌ መስተንግዶ አገልግሎት 0.5 %) 10084.80

የውል ማስከበሪያ 1% በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ በጤና ጣቢያው ስም ተሰርቶ ማምጣት ይጠበቅበታል በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች ተሞልተው ሰነዱ ተፈርሞበትና የድረጅቱ ማህተም ተደረጎበት ይመለሳል፤ለጥቃቅን ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ ከአደራጃችሁ ተቋም ማምጣት ይኖርባችሁዋል፡፡ ሙሉ ሰነዱ ላይ ፊርማ እና ማህተም ተደርጎ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች ተሞልተው ኮፒ ተደረጎ ከኮፒው ጋር ሲፒኦ ማሲያዝና መመለስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ጨረታው በ11ኛ ቀን 4፡00 ሠአት ተዘግቶ 4፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጤና ጣቢያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል በማንኛውም ምክንያት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ወድቅ ይሆናል።መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

አድራሻ ከኮካ አደባባይ ወደ መሣለሚያ ወይም ከመሣለሚያ ወደ ኮካ አደባባይ በሚሄደው ዋና መንገድ ሲሄዱ የቀድሞ 24 ቀበሌ መዝናኛ ክበብ ፊት ለፊት ባለው ዳገታማ መንገድ 200 ሜትር እንደሄዱ በሚታየው ባለ አራት ፎቅ ህንፃ ላይ ያገኙናል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0118-27-56 08 ወይም 0118-27-90-60

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 03 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን 4፡00 ሠአት
  • Bid opening: 2026-08-07 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን 4፡30 ሠአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ketema Sub City Wereda 3 Health Post
  • Buyer address: ከኮካኮላ አደባባይ ወደ መሣለሚያ ወይም ከመሣለሚያ ወደ ኮካኮላ አደባባይ በሚወስደው ዋና መንገድ ሲሄዱ የቀድሞ 24 ቀበሌ መዝናኛ ክበብ ፊት ለፊት ባለው ዳገታማ መንገድ 200 ሜትር እንደሄዱ በሚታየው ባለ 4 ፎቅ ህንፃ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T07:38:10.000Z
← Back to all tenders