Property and building foreclosure

በሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ፍ/ቤት በ500 ካሬ ሜትር ላይ ያለውን የመኖሪያና የኪራይ ቤት ቤትና ቦታ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ አውጥቷል

Description

የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ላቀች በጋሻው እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ማሚታ የኋላሸት መካከል ባለው የአፈፃፀም ክርክር የፍርድ ባለዕዳና ባለመብት ተስማምተው በውሳኔ ያገኙትን ቤትና ቦታ ለመጠቀም ያልቻሉ በመሆኑ መነሻ ዋጋው አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ አስራ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ስድስት ብር ከሰላሳ አራት ሳንቲም የሆነውና በ500 ካሬ ሜትር ላይ ያለውን በሰ/ሸዋ ዞን ጣ/በር ወረዳ በደ/ሲና ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ቦታው ምንተዚሞ አዋሳኙ በምስራቅ ዘውድነሽ በላይ፣ በምዕራብ እቴነሽ ተክሌ፣ በሰሜን የወጣቶች መናፈሻ እና፣ በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኘው ስምንት ክፍል የመኖሪያና የኪራይ ቤት ቤትና ቦታ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡ የጨረታ ማስታወቂያውን በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከሀምሌ 20/2018 እስከ ነሀሴ 20/2018 ድረስ እንዲቆይ ከተደረገ በኋላ ጨረታው በነሀሴ 20/2018 ንብረቱ በሚገኝበት ስፍራ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ይከናወናል ንብረቱ በሚገኝበት በግልፅ ጨረታ ስለሚሸጥ ተጫራቾች/ወኪል/ ግምቱን 1/4 ለሀራጅ ባይ በማስያዝ ተጫርታችሁ መግዛት የምትችሉ ሲሆን ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች የሚመለስና ለአሸናፊዎች ታሳቢ ሆኖ ገንዘቡን በ15 ቀን ውስጥ አጠናቀው ገቢ ማድረግ ያለባቸው መሆኑን ያሳውቃል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Shewa Zone Tarmaber Woreda Court
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T07:51:38.000Z
← Back to all tenders