Property and building foreclosure
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ የሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሰንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ የሀራጅ ጨረታ እወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (በአስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ይመለስላቸዋል::
- ተበዳሪው/ መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት ጨረታ በሚካሄድበት ቦታ መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ገዥ ይከፍላል:: ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ እዳ ደግሞ ወደ አሸናፊው/ገዥው የሚተላለፍ ይሆናል::
- የጨረታው አሸናፊ ንብረቱ በሚገኝበት የከተማ አስተዳደር ወይም ወረዳ አስተዳደር ዘንድ ቀርቦ ባሸነፈበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብርና ታክስ ይከፍላል::
- የጨረታው አሸናፊዎች ለመንግሥት የሚከፈለውን የ15% (የአስራ አምስት በመቶ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ ይከፍላሉ::
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት የሚቻል ሲሆን፣ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 046-212-1710 እና በ046-212-2346 ሀዋሳ በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ዓ.ም. |
የተጫራቾች ምዝገባ ሰዓት |
የጨረታው ሰዓት |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ንብረቱ በሚገኝበት |
የንብረቱ ኣገልግሎት |
የቦታው ስፋት (በካ.ሜ) |
የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር |
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
|
1 |
አቶ ኢሳያስ ዳሌ |
አቶ ብርሃኑ ኃይሉ ወልደማርያም |
ሲዳማ ብ/ክ/መ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ታቦር ክ/ከተማ፣ ሂጣታ ቀበሌ |
5,122,162.66 |
ነሃሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:00- 5፡00 ጠዋት |
5:01- 5:30 ጠዋት |
ሀዋሳ ከተማ፣ታቦር ክ/ከተማ፣ አቢሲንያ ባንክ አሊቶ ቅርንጫፍ |
ለመኖሪያ |
376.84 ካ.ሜ |
1135 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
2 |
አቶ ከማል ሀሰን አራርሶ |
ወ/ሮ አሊያ ከድር ጫካ |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ፣ምዕራብ አርሲ ዞን፣ ሻሸመኔ ከተማ፣ አለቼ ክ/ከተማ፣አዋሾ ወረዳ |
3,879,134.06 |
ነሃሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:00- 5፡00 ጠዋት |
5:01-5:30 ጠዋት |
ሻሸመኔ ከተማ አለቼ ክ/ከተማ፣ አቢሲንያ ባንክ አዋሾ ቅርንጫፍ |
ለመኖሪያ |
146.46 ካ.ሜ |
LHC NO- 22092912 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
3 |
አቶ ከማል ሀሰን አራርሶ |
አቶ ከማል ሀሰን አራርሶ |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ፣ምዕራብ አርሲ ዞን፣ ሻሸመኔ ከተማ፣አለቼ ክ/ከተማ፣አዋሾ ወረዳ |
3,190,299.86 |
ነሃሴ 22 ቀን 2018 ዓ.ም |
8:00- 9፡00 ከሰዓት |
9:00- 9፡30 ከሰዓት |
ሻሸመኔ ከተማ፣አለቼ ክ/ከተማ፣ አቢሲንያ ባንክ አዋሾ ቅርንጫፍ |
ለመኖሪያ |
140 ካ.ሜ |
LHC NO- 18490 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
4 |
አቶ ዮሐንስ ስለሺ |
ወ/ሮ ቦጋለች |
ኦሮሚያ ብ/ክ/መ፣ ያቤሎ ከተማ፣ 02 ቀበሌ |
800,216.60 |
ነሃሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም |
8:00- 9፡00 ከሰዓት |
9:00- 9፡30 ከሰዓት |
ያቤሎ ከተማ፣ አቢሲንያ ባንክ ያቤሎ ቅርንጫፍ |
ለመኖሪያ (G+0) |
226.50 ካ.ሜ |
LHC NO- 341/2010 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
|
5 |
ገናሌ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/ የግ/ማ |
መኩሪያ ባሳዬ |
ሲዳማ ብ/ክ/መ ሐዋሳ ከተማ፤ አዲስ ክ/ከተማ፤ ዳካ ቀበሌ |
44,118,562.37 |
ነሃሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:00-5:00 ጠዋት |
5:01-5:30 ጠዋት |
ሀዋሳ ከተማ አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ሐዋሳ ዲስትሪክት ጽ/ቤት 4ኛ. ፎቅ |
ጅምር G+3 የንግድ ሕንጻ |
3,800.00 ካ.ሜ |
6565 |
ለሁለተኛ ጊዜ |
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-03 11:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T10:54:34.000Z