Stationery and office consumables
ዋስ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የ ጨ ረ ታ ማ ስ ታ ወ ቂ ያ
ዋስ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን የተለያዩ ብዛት ያላቸው ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል.
|
ተ.ቁ |
የእቃው ዝርዝር |
ጥቅል(Lot) |
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ |
|
1 |
የኮምፒውተርና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
ጥቅል 1 |
500 birr |
|
2 |
የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች |
ጥቅል 2 |
500 birr |
በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- እያንዳንዱ ተጫራች ከላይ በጥቅል ከተከፋፈሉት ዝርዝሮች ውስጥ በነጠላ ወይም በሁለቱም Lot (ጥቅል) መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ከተጫራቹ ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% መሆን አለበት፤ ሆኖም መጠኑ ከብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በታች መሆን አይችልም። ተጫራቹ በእነዚህ ሁለቱ መስፈርቶች መሰረት ከፍተኛዉን መጠን በጨረታ ማስከበሪያ መልክ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ከአንድ ጥቅል በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የሚወዳደሩበትን ጥቅል ሰነድ መግዛት የሚኖርባቸው ሲሆን ሰነዶቻቸውን ሲመልሱ በየጥቅሉ በመነጣጠል ለየብቻ በማድረግ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በየጥቅሉ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በኩባንያችን ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከተጠቀሰው መጠን በታች ያስያዘ ተጫራች ከጨረታ ውጭ የሚደረግ ይሆናል።
- ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት ስታድየም ከናሽናል ታወር አጠገብ በሚገኘው የዋስ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋናው መ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01-D2 ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ ለየጥቅሉ የተገለፀውን ክፍያ በኩባንያዉ የሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ10:30 በኩባንያው ዋና መ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01-D2 ይከፈታል።
- ለበለጠ መረጃ ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 09-95-37-20-14 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ዋስ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት
ስታድየም ናሽናል ታወር አጠገብ አን ቢዝነስ ሴንተር አንደኛ ፎቅ
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-07-31
- Bid closing time: 16:00
- Bid opening: 2026-07-31 16:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Was Insurance S.C.
- Buyer address: ኦሎምፒያ ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ NK Building 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 306 እና 307
- Bid bond: 2% ሆኖም መጠኑ ከብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በታች መሆን አይችልም
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T11:09:39.000Z