Disposal, scrap and surplus sales

ቡና ባንክ አ.ማ. ሲገለገልባቸው የነበሩትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ንብረቶችን እና የፅህፈት መሣሪያዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ቡባ/ፋማዳ/ሽጨ/010/26

ቡና ባንክ አ.ማ. ሲገለገልባቸው የነበሩትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ንብረቶችን ፤ የፅህፈት መሣሪያዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የጨረታ ሰነዱ መግለጫዎች

1. ንብረቶቹን መግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ወሎ ሰፈር አደባባይ ጋራድ ህንፃ B(ቢ.)ታወር 7ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ነሐሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ ወይም የባንኩን የዲጅታል አማራጮች በመጠቀም በሂሳብ ቁጥር 1019601000609 ለየምድቡ ዕቃዎች የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ገቢ በማድረግ እና ገቢ የተደረገበትን ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት እስከ ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸው:: የጨረታው ሳጥን በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ጋራድ ህንፃ B(ቢ.)ታወር 7ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በቡና ባንክ አ.ማ.ወይም “Bunna Bank s.c. ስም በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታ አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%)የመክፈል ግዴታ አለበት።

5. የጨረታው አሸናፊ የጨረታ ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ክፍያ በመፈፀም ንብረቶቹን ከባንኩ መረከብ ይኖርበታል:: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ተደርጎ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል።

6. ንብረቶችን መመልክት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው አድራሻ መሠረት መመልከት ይችላል።

7. ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስየዙትን ገንዘብ የጨረታው ውጤት በተገለፀ ከአምስት ቀናት በኋላ መውሰድ ይችላሉ።

8. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁ 011-126-43-67 / 011-557-72-91 / 011-126-19-01 መጠቀም ይቻላል።

ቡና ባንክ

የባለራዕዮች ባንክ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-13
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-13 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bunna Bank S.C.
  • Bid bond: 5,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር ለየምድቡ
  • Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T12:15:28.000Z
  • Buyer website: https://bunnabanksc.com/
← Back to all tenders