Stationery and office consumables

የአርሲ ዞን ሥሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለአገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019

የአርሲ ዞን ሥሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለአገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ ፈርኒቸር፤ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡

1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.)ያላቸው እና በፌዴራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፤ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች፤ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በጽ/ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000062690023 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የፋይናንስ አስተዳደር የሥራ ጉዳይ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።

5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎችእና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15000.00 (አሥር አምስት ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ስነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000.00 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ(C.P.O.) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል።

6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ሥሬ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።

7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022 380 0408/0913 910 056/0913 519 264 ይጠይቁ።
የአርሲ ዞን ሥሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-13
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-13 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Arsi Zone Sire Woreda Finance Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T12:58:39.000Z
← Back to all tenders