Property and building foreclosure
የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሔር ጉዳይ ችሎት የመኖሪያ ቤት መሸጥ ይፈልጋል
Description
ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት ዶ/ር ሀይለልዑል ዘለቀ እና በፍርድ ባለዕዳ ወ/ሮ ራሔል አለማየሁ እና በአመልካች የፌዴራል ገቢዎች ጽ/ቤት አዳማ ቅርንጫፍ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክርክር በተመለከተ በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ጎሮ ውስጥ የሚገኝ ፣ 200 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ሰፍሮ የሚገኝ የካርታ ቁጥር 5079/95 በ18/05/2003 የተሰጠ በፍርድ ባለዕዳ ወ/ሮ ራሔል አለማየሁ ዋሴ ሥም ተመዝግቦ የሚታወቅ የመኖሪያ ቤት በጨረታ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 3,677,680.20 (ሶስት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ ብር ከ20/100) በሆነ በ22/12/2018 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በግልጽ ጨረታ ይሸጣል።
ተጫርቶ መግዛት የሚፈልግ ሰው ካለ ለአፈጻጸሙ ምክንያት የሆነውን ቤት የጨረታ መነሻ ዋጋ ግምት ¼ ኛ አስይዞ ሲፒኦ ይዞ ጨረታው ይካሄዳል በተባለበት ቀን እና ሰዓት በቦታው በመገኘት ተጫርቶ መግዛት የሚችል መሆኑን እናስታውቃለን።
የአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሔር
ጉዳይ ችሎት
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-08-28 12:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama City Higher Court
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Jul 27, 2026)
- Posted at: 2026-07-27T13:47:12.000Z