Stationery and office consumables
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት የሚዉሉ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 1
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት ዓመት ለከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት የሚዉሉ
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 4 የደንብ ልብስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፍርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሱ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1. ህጋዊ የታደስ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ
3. የግብር ከፍያ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው
4. የድርጅቱ ሀጋዊ ማህተም ያለው
5. የገንዘቡ መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ ብር / እና ከዚያም በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ከፋይነት የተመዘገበ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለጽህፈት መሳሪያ 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/፣ ለኤሌክትሮኒክስ/54000/ሀምሳ አራት ሽህ ብር/ለጽዳት እቃ 5000/አምስት ሺህ ብር/ ለቋሚ መሰል ዕቃ 10,000/አስር ሺህ ብር/የደንብ ልብስ 15000 /አስራ አምስት ሺህ/ ለጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋት 3፡30/ሶስት ሰዓት ተኩል ድረስ/ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥናፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 3፡31/ሶስት ከሰላሳ አንድ ተዘግቶ 4፡00/አራት ሰዓት /ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ውስጥ ይከፈታል፡፡
8. የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፌኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 የሰነድ ክፍያ በመፈጸም የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 07 ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑ ይታወቃል።
11. ጨረታው ተሳታፊዎችን ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ማህተም የሌላቸው ተጫራቾች ህጋዊ ፊርማችሁን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
12. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው።
13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ዐ6 ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልሳዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋት 3፡31/ሶስት ከሰላሳ አንድ/
- Bid opening: 2026-08-12 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋት 4፡00/አራት ሰዓት/
- Region: Amhara
- Publishing entity: በሰሜን ሸዋ ዞን የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ / ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T08:14:03.000Z