Stationery and office consumables
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶችና የአገልግሎት ግዥዎች (የኮምፒዩተርና ተዛማጅ የቢሮ ዕቃዎች ጥገና እና የተሽከርካሪ ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት
- የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሌሎች አላቂ ዕቃዎች
- ቋሚ ዕቃዎች ፤
- የጽዳት ዕቃዎች፤
- የደንብ ልብሶችና የአገልግሎት ግዥዎች
- (የኮፒዩተርና ተዛማጅ የቢሮ ዕቃዎች ጥገና እና የተሽከርካሪ ጥገና)
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡
- ዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000/ ከሁለት መቶ ሺህ ብር / በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው።
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም።
- የጨረታው አሸናፊ ውል ከያዙበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ቀናት ውስጥ እቃውን ገቢ ማድረግ አለበት ፤በተጠቀሰው ቀን ውስጥ እቃውን ገቢ ማድረግ ካልቻለ የጨረታው አሸናፊ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ ገንዘብ የሚወረስ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ከፎቶ ኮፒና ከኦሪጅናል መጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፤እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ አርዕስት ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 15,000.00 / አስራ አምስት ሺህ ብር/ ቢድ ቦንድ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሰርቲፋይድ ቼክ /CPO/ለማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር 09 ድረስ ቀርበው በመውሰድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሚሸጡበትን ዋጋ ዋናውንና ኮፒውን በደንብ በታሸገ ፖስታ በጽ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡የዕቃው ጥራት በተገለፀው ስፔስፍኬሽንና በሳምፕሉ መሰረት በመ/ቤቱ ባለሙያዎች የሚመረጥ ይሆናል፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን በኮሚቴ መከፈት አያግደውም፡፡ የሚከበሩ የህዝብ በአላት ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
ጽ/ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል።
ለተጨማሪ መረጃ
ቀበሌ13 ወጣቶች ጎን አዲሱ መንታ ህንፃ ሚዛኒ ቢሮ ቁጥር 9
ስልክ ቁጥር 058-222-19-99
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና
አስተዳደር ሰሜን ምዕራብ ሪጅን
ባህርዳር ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-07
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-07 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የመንግሥት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ሰሜን ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት
- Bid bond: 15,000.00 ብር በየሎቱ
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T08:23:32.000Z