Stationery and office consumables

የአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በሥሩ ለሚተዳደሩ ባለበጀት መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በሥሩ ለሚተዳደሩ ባለበጀት መ/ቤቶች የተለያዩ

  1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  2. የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች
  3. ቋሚ አላቂ ዕቃዎች
  4. የፅዳት ዕቃዎች
  5. ፈርኒቸሮች
  6. የመኪና ጎማ
  7. የደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ እስከ አያቱድ 8. ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ የሚያቀርቡበትን የመጓጓዣ፣ ማስጫኛ እና ማውረጃ ወጪን በመጨመር ከዚህ በታች በተጠቀሰው ሁኔታ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

1. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በክልል ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በሚጫረቱበት ዘርፍ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ።

2. ተጫራቾች የ2018/2019 ዓ.ም ግብር የከፈሉና ለዚህም የንግድ ሥራ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ስለመሆናቸው እና ማህሐ ሰርትፍኬት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸወል።

3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 21/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አሰተዳደር ክፍል ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 – 11፡30 ሰዓት ድረስ የሚሸጥ መሆኑን እንገልጻለን።

4. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ከ መ/ቤቱ ግዥ ና ንብረት አስተዳደር ክፍል መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች 5,000.00 (አምስት ሺህ) ብር ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድቦንድ ለያንዳንዱ ሰነድ ልክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፐኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አስገብተው ከ ኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በጥራት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመስሪያ ቤቱ ጥያቄ መሠረት ብቻ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ ሙሉ አድራሻቸውን ና የተወዳደሩበትን ዕቃ ዓይነት በመጥቀስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት አዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ገንዝብ ጽ/ቤት ይከፈታል።

8. ተጨራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች የማስረከቢያ ቦታ አዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ገንዝብ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ (እስቶር) ውስጥ መሆኑን ውስጥ መሆኑን እንገልጻለን።

9. ተጫራቾች ከ20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር እና በላይ ዕቃ የሚፋጸመው የግዥ ከፊያ 3% (with holding) እና ተጨማር ኢስትታክስ ወይም ቫት 7.5 ፕረስነት 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ተቆርጦ ለመንግስት ገብ እነደሚሆን ማወቅ አለባቸው።

10. ተጫራቶች ከ 200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ለሚያቀርቡት ዕቃ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች እየዳኑትን የጨረታ አይነት በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ አሽጎ አድራሻ ስልክ ቁጥር በትክክል ለይተው በመጸፍ ማቅረብ ይኖርበቸዋል።

12. ማንኛውም አቅራቢ ከመንግስት ግዥ ከታገደ በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም።

13. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ለይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሸል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም።

14. ጽ/ቤታችን የሚያመርታቸውን ዕቃዎች ብዘት 2ዐ እንደ አስፈላጊነታቸው በመጣር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።

15. የሚገዙ ዕቃዎች በተው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሞልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጸም ሀላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው።

16. ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ በሆኑበት ዕቃ ለ3 ወር የዋጋ ለውጥ ሳይደረግ ባሸነፉበት ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

17. ተጨራቾች የሚያቀርበቸው ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ኦርጅናል መሆን ይኖርባቸዋል።

18. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በአምስት (5) ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ በጫረታው ውጤት ለይ ቅሬታ ማቅረብ ይችላል።

19. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን ዕቃ አይነት በነጠላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።

20. ተጨራቶች ሳምፒል እንዲያቀርቡ የተጠየቀውን ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

21. ጨረታውን ለማስተጓጓል የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆንና ለወደፊት በማንኛውም ጨረታ እንዳይወዳደር ይደረጋል።

22. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ መሆኑን እንገልጻለን።

23. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው እቃዎች አሸናፊ መሆናቸው ሲገለጽላቸው ለውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

24. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ውል መግባት አለበት።

25. አሸናፊው ድርጅት ውል በገባ በ10 ተከታታይ ቀን ውስጥ እቃውን በማቅረብ ገቢ ማድረግ የሚጠበቅበት ሲሆን በተበለው ቀናት ውስጥ ሳያስገባ ቢቀር ውል ሰጪው ህጋዊ ርምጃ መውሰድ እንደሚችል መረዳት ይኖርበታል።

ማሳሰቢያ

  • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በባዓልና በዝግ ቀናት ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ላይ ይሆናል/ይውላል።
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-441-24-47 ወይም 046-441-27-31 የአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጠየቅ ይቻላሉ።

 የአዳሚ ቱሉ ጅዶ ኮምቦልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-14
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-14 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adami Tulu Jido Kombolcha Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 5000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
  • Posted at: 2026-07-28T08:41:35.000Z
← Back to all tenders