Property and building foreclosure

የቤት የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

Description

የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈ / ከሳሽ ፀደይ ባንክ ወልዲያ ቅርንጫፍ ነፈጅ ሙሉጌታ አስራት እና በአፈ ተከሳሽ 1ኛ/ ፈንታ ማርየ 2ኛ/ ዘገየ ተካ 3ኛ/ ዘገየ ማርየ 4ኛ/ ጦይባ መሀመድ 5ኛ/ ዚነት መሀመድ 6ኛ/ ጥሩ መንግስቴ 7ኛ/ አዲሴ ሞላ 8ኛ/ አሸቱ ይመር 9ኛ ደርበው ዘውዱ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በጉባላፍቶ ወረዳ 05 ቀበሌ በዶሮ ግብር ከተማ ቀበሌ በ6ተኛ አፈ ተከሳሽ እና በአቶ ተገኝ አብርሃ ስም በካርታ ቁጥር 103 በሆነው ተመዝግቦ የሚገኘውና አዋሳኙ፡-

  • በምስራቅ ....ሞላ አባሀምሌ
  • በምዕራብ.... ዋጋየ ይመር
  • በሰሜን........ መንገድ
  • በደቡብ…… መንገድ የሚያዋስነው ቤት ከዕዳና እገዳ ነፃ መሆኑ ታውቆ ቤቱን ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በሀራጅ ጨረታ እንዲሸጥ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። ስለዚህ የጨረታው ማስታወቂያው ከሀምሌ 21 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ነሀሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ 30 ቀን አየር ላይ ቆይቶ ጨረታው ነሀሴ 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ ይካሄዳል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ መግዛት የሚፈልግ በጉባላፍቶ ወረዳ 05 ቀበሌ በዶሮ ግበር ከተማ ለጨረታ በወጣው ቤት ግቢ ውስጥ በመገኘት መግዛት/መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታው አሸናፊ የጨረታ አሸናፊነቱን እንዳወቀ ወዲያውኑ ሀያ አምስት በመቶውን በሰሜን ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስም በተከፈተው የአደራ ገንዘብ ማስቀመጫ አማራ ባንክ ወልዲያ ሂሳብ ቁጥር 9900005450938 በሆነ እንድታስይዙ ደረሰኙን ለሀራጅ ባይ ወዲያውነ እንደሰጠ እና ቀሪ ብሩን በአስራ አምስት ቀን ውስጥ ከፍሎ ማጠናቀቅ ያለበት መሆኑን እናሳውቃለን።

የሰሜን ውሎ ዞን ዞን ከፍ/ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-08-27 09:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Wollo Zone High Court
  • Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
  • Posted at: 2026-07-28T08:48:28.000Z
← Back to all tenders