Stationery and office consumables
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 3 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር Y/S/C/W/3/Fin.NCB001/2019 ዓ.ም.
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 3 ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ዙር በወረዳው የተለያዩ ፅ/ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ
- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ፣
- የፅዳት ዕቃዎች ፣
- የደንብ አልባሳት ፣
- የተለያዩ ቋሚ ዕቃ፣
- የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች ፣
- የተለያዩ ህትመት አገልግሎት፣
- የተለያዩ መስተንግዶ አገልግሎት፣
- የህዝብ ትራንስፖርት፣
- የጭነት ትራንስፖርት፣
- የተለያዩ የልብስ ስፌት ፣
- የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ፣
- የፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት፣
- የሞንታርቦ ኪራይ አገልግሎት ፣
- የጄኔሬተር ኪራይ አገልግሎት ፣
- የድንኳን ኪራይ አገልግሎት እና
- የዲኮር ኪራይ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡-
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
|
የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን |
|
|
001 |
የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች |
ናሙና የሚቀርብበት |
10000 |
00 |
|
002 |
የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች |
ናሙና የሚቀርብበት |
10000 |
00 |
|
003 |
የተለያዩ ደንብ አልባሳት |
ናሙና የሚቀርብበት |
10000 |
00 |
|
004 |
የተለያዩ ቋሚ ዕቃ |
ናሙና በከለር ፎቶ የሚቀርብ |
10000 |
00 |
|
005 |
የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች |
ናሙና በከለር ፎቶ የሚቀርብ |
10000 |
00 |
|
006 |
የተለያዩ ህትመት |
ናሙና የሚቀርብበት |
5000 |
00 |
|
007 |
የተለያዩ መስተንግዶ |
የአገልግሎት ዘመኑ ቅርብ የሆነ |
5000 |
00 |
|
008 |
የህዝብ ትራንስፖርት ኪራይ |
ጥራቱን የጠበቀ የተስተካከለ |
5000 |
00 |
|
009 |
የጭነት ትራንስፖርት ኪራይ |
ጥራቱን የጠበቀ የተስተካከለ |
5000 |
00 |
|
010 |
የተለያዩ የደንብ አልባሳት ልብስ ስፌት |
ጥራቱን የጠበቀ ስፌት |
5000 |
00 |
|
011 |
የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት |
ጥራቱን የጠበቀ ጥገና |
5000 |
00 |
|
012 |
የፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት |
ጥራቱን የጠበቀ ጥገና |
5000 |
00 |
|
013 |
የሞንታርቦ ኪራይ አገልግሎት |
ጥራቱን የጠበቀ የተስተካከለ |
5000 |
00 |
|
014 |
የጄኔሬተር ኪራይ አገልግሎት |
ጥራቱን የጠበቀ የተስተካከለ |
5000 |
00 |
|
015 |
የድንኳን ኪራይ አገልግሎት |
የተለያየ ጥራቱን የጠበቀ |
5000 |
00 |
|
016 |
የዲኮር ኪራይ አገልግሎት |
ጥራቱን የጠበቀ ያልተቀደደ |
5000 |
00 |
ስለዚህ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው
ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።
ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የተመዘገበ መሆን አለባቸው።
በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችልና በወቅቱ በማንኛውም ሁኔታ ያልተቀጣ (እንዲወዳደር ያልታፃደ) መሆን አለበት።
በዚህ ጨረታ አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን ከሎት 001 እስከ ሎት 005 ለተዘረዘሩት ብር 10000.00 አስር ሺህ ብር/ ከሎት 006 እስከ ሎት 016 ለተዘረዘሩት ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው ሎት ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 3 ፋይናንስ ፅ/ቤት ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል/ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ ማቅረብ አለበት።
- ማንኛውንም ተጫራች የሚያስገባው ሰነድ የጨረታ ሰነድ ላይ ፣ ስርዝ ድልዝ ፤ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ፣ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ፅ/ቤት ልዩ ቦታው ቤላ ጣሊያን ኤምባሲ አጠገብ በሚገኘው የአስተዳደሩ ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፤
- በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ፋይናሻልና ቴክኒካል ሰነዶች ተገምግመው አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን የፅህፈት መሳሪያ፤ የፅዳት ዕቃ፣ የደንብ አልባሳት ቋሚ ዕቃ ሙሉ ለሙሉ አዘጋጅቶ ገቢ ከማድረጉ በፊት ከየዓይነቱ ናሙና ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ቤላ ጣሊያን ኤምባሲ አጠገብ በሚገኘው የወረዳ 3 አስተዳደር 1ኛ ፎቅ ግዢ የስራ ሒደት ቢሮ ቀርበው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በወረዳው ግዢ የስራ ሒደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 012 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 1ኛ ፎቅ ትንሹ ቢሮ ቁጥር 012 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተራ ቁ 6 ላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ፡- ከጣሊያን ኤምባሲ ፊት ስፌት በስተቀኝ ኮብልስቶን መንገድ 60 ሜትር ገባ ብሎ
በስ/ቁጥር፡- 0111 22 19 88 /0111 54 47 72
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-08
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-08 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yeka sub City Admnistration woreda 03 finance & Development Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T09:21:01.000Z