South West Ethiopia Region
የካፋ ልማት ማህበር የቆዩ አሮጌ ተሽከርካዎችንና ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሎት በማከፋፈል በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የካፋ ልማት ማህበር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ በማህበሩ የእንግዶች ማረፊያ ተቋም እና በኃኪዮን የመኪናዎች ጥገናና ሰርቪስ ጋራዥ ግቢ ውስጥ እና በቦንጋ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ በተለያዩ ጊዜያት አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ አሮጌ ተሽከርካዎችንና ልዩ ልዩ ንብረቶችን በሎት በማከፋፈል በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት-
- ሎት 1 ያገለገለ አሮጌ ማርቸዲስ መኪና
- ሎት 2 ያገለገለ አሮጌ ዲፌንደር መኪና
- ሎት 3 ያገለገለ አሮጌ ዶዘር
- ሎት 4 አሮጌ የተለያዩ ብረታ ብረቶች በኪሎ ግራም
በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካፋ ልማት ማህበር ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አካውንት ቁጥር 1000029065695 ገቢ በማድረግ በካፋ ዞን በቦንጋ ከተማ በካፋ ልማት ማህበር ሕንፃ ቁጥር 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ቀርቦ የጨረታ ዶክመንቱን ለተከታታይ 15 ቀናት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ሎቶች ማለትም ለሎት 1፣ ለሎት 2 እና ለሎት 3 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በቼክ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ እንዲሁም ለሎት-4 ማለትም ለአሮጌ የተለያዩ ብረታ ብረቶች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በጥሬ ገንዘብ ወይንም በቼክ ብር 30,000.00 /ሠላሳ ሺህ ብር/ በካፋ ልማት ማህበር ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ኦሪጅናል የጨረታ ዶክመንት ላይ ተገቢውን አድራሻ ማለትም ሥም እና ስልክ ቁጥር በመፃፍ እና ፊርማ በማሳረፍ እንዲሁም ማንነትን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ካርድ ኮፒ በማያያዝ ለየብቻ በሰም /በሙጫ/ በታሸጉ ፖስታዎች በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ልማት ማህበር ሕንፃ ቁጥር 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከመግዛታቸው በፊት ተሽከርካሪዎቹ እና የተለያዩ ሌሎች አሮጌ ዕቃዎች የሚገኙበትን ሁኔታ በቦታው ቀርቦ ማየት ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ልማት ማህበር ሕንፃ ቁጥር 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል:: የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለውየሥራ ቀን ይሆናል።
- የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
- 15 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ የሚቆጠር ነው።
- ተጫራቾች አሰሪው ቤት ያዘጋጀውን የፋይናንሻል ዶክመንት መጠይቅ በአግባቡ ሞልቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራች ግዢውን ከመፈጸሙ በፊት ክፍያውን ሙሉ በሙሉ በካፋ ልማት ማህበር ባንክ አካውንት ቁጥር 1000029065695 በማስገባት አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በተከታታት 7 ቀናት ውስጥ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ስሊፕ ማቅረብ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቀጥር 0473310420
ሞባይል ቁጥር 0917534381 ወይንም 0911596829 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የካፋ ልማት ማህበር
ቦንጋ፣
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-12 10:30
- Bid opening (note): የጨረታው ሳጥን በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Kefa Development Association
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
- Posted at: 2026-07-28T09:35:42.000Z