Property and building foreclosure

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍ/ቤት ቤት መሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአፈጻጸም ከሳሽ አብሮ አደግ እቁብ ማህበር እና በአፈጻጸም ተከሳሽ አቶ ይርጋ ፈቃዱ መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈጻጸም ተከሳሾች በፍርድ ቤቱ መሰረት መፈጸም ባለመቻላቸው ምክንያት፤ የአፈጻጸም ተከሳሽ ንብረት የሆነው በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 ተመዝግቦ የሚገኘው፣ በምስራቅ ንብረት፣ በሰሜን አንሙት ታደሰ ፣በምእራብ ዳዊት ዘለቀ፣ እንዲሁም በደቡብ መንገድ ተዋስኖ የሚገኘው፤ በአቶ ይርጋ ፈቃዱ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ቤት በመነሻ ግምቱ 2‚496‚808 (ሁለት ሚሊዩን አራት መቶ ዘጠና ስድስት ሽህ ስምንት መቶ ስምንት ) ብር በጨረታ ይሸጣል። የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ድረስ ጨረታው ይከናወናል። በመሆኑም ተጫራቾች የግምቱን ¼ኛውን ገንዘብ ቀድመው በሲፒዩ አስይዘው በእለቱ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል።


የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-08-27 11:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Guagesa Skudade Woreda Court
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T06:32:58.000Z
← Back to all tenders