Disposal, scrap and surplus sales

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ኮካ ኮላ ፋብሪካ ጎን ከሚገኘዉ ሸድ የተለያዩ ያገለገሉ የስፌት ማሽኖችን፣ የተዘጋጁ ልብሶችን፣ ጣቃ ልብስና ሌሎች ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ኮካ ኮላ ፋብሪካ ጎን ከሚገኘዉ ሸድ የተለያዩ ያገለገሉ የስፌት ማሽኖችን፣ የተዘጋጁ ልብሶችን፣ ጣቃ ልብስና ሌሎች ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

 ስለዚህ ያለምንም ፈቃድ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. የሚሸጡ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ወይም ከሸዱ በአካል በመሄድ ማየት ይቻላል።
  2. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ክፍል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 2.30 - 11.30 ድረስ በ20ኛዉ ቀን ስነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ መ/ቤቱ ገንዘብ ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አብክመ ኢፖልኮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አብክመ ኢፖልኮ 21ኛ ቀን 3፡30 ይታሸግና 4፡00 ይከፈታል። ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 3፡30 ይታሸግና 4፡00 ይከፈታል።
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 4767 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  8. ሌሎች በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ በኮርፖሬሽኑ የግዥ መመሪያ መሰረት ይስተናገዳሉ።

የአማራ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-17
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛ ቀን 3፡30
  • Bid opening: 2026-08-17 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21ኛ ቀን 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Industry Parks Development Corporation
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T06:51:44.000Z
← Back to all tenders