Property and building foreclosure
72 ካ.ሜ ስፋት ያለው G+3 ህንፃ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት አቶ ማአሾ ግደይ እና በፍርድ ባለእዳ ሻምበል ፍረወይኒ አርአያ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 32631 በቀን 26/06/2018 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 155086 በቀን 12/9/2018 ዓ.ም፣ 27/9/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 4 በሟች ግደይ ገ/ዋህድ ስም የሚታወቅ በምስክር ወረቀት ETH0001009000-00004171532 በልዩ መለያ ቁጥር AA000090408493 የተመዘገበ 72 ካ.ሜ ስፋት ያለው G+3 ህንፃ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 7,656,516 (ሰባት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሀምሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ አስራ ስድስት ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል
የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የስራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ ቤት C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ
አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-01 10:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T08:14:04.000Z