Stationery and office consumables

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምስራቅ ጎህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምስራቅ ጎህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ፡-

  •  ቋሚ ዕቃዎች፣
  •  የፅህፈት መሳሪያ፣
  • የደንብ ልብስ፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣
  •  አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣
  • የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
  • የተለያዩ የህፃናት መጫወቻ ዕቃዎች፣
  • የላብራቶሪ ዕቃዎችና
  •  የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታ የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1.  የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለዚህም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2.  በመንግስት ንብረት ግዥ አስተዳደር ኤጄንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (vat) ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4.  የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  5. ክሊራንስ፦ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀና ለዚህም ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በት/ቤቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን(ግዥ ክፍል) ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በግልፅ መሙላት አለባቸው ይህን ያላደረጉ ተጫራቾች ቫትን አካተው እንደሞሉ ይቆጠራል፡፡
  10. ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር የስራ ሰአት በ/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  11. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ) ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ላይ በት/ቤቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
  12. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ካዛንችስ ቶታል ፊት ለፊት ወደ አዋሬ መሄጃ መንገድ ምስ/ጎህ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 0115-15-56-52

ምስራቅ ጎህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-10 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Misrak Goh General Secondary School
  • Bid bond: 2% በየሎቱ
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T08:22:28.000Z
← Back to all tenders