Building and equipment maintenance
የድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የአጥር ጥገና፣ የመስኮት ጥገና እና የመምህራን ማረፊያ ሶፋ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ቁጥር 01/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በውስጥ ገቢ በጀት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትይፈልጋል፡፡
- ሎት 1፡- የአጥር ጥገና
- ሎት 2፡- የመስኮት ጥገና
- ሎት 3፡- የመምህራን ማረፊያ ሶፋ ጥገና
በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተወዳዳሪዎች፡-
- በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- በጥቃቅን እና አነስተኛ በአምራችነት ተደራጅተው የሚመጡ ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል።
- የእቃዎች ዋጋ 15% ቫት ተጨምሮ ይቅረብ፣ ባይቀርብ እንደተጨመረ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ መሙላት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሎት1፡15,000.00 ለሎት2፡15,000.00 ለሎት3፡15,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተመረጡ እቃዎች እና ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን በቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጭ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማምጣት አለባቸው፡፡ ት/ቤቱ ተጨማሪ የስራውን 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት 10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 01የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፦ ጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮሜዳ ከስፔን ኤምባሲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0111-54-20-95
የድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛ
እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-08
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት 10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-10 09:30
- Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት 11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Del Betegel Elementary School
- Buyer address: ጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮ ሜዳ ከስፔን ኤምባሲ አጠገብ
- Bid bond: 15,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T08:27:29.000Z