Property and building foreclosure
የቦታው ስፋት 200 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት እና ቦታ 65 (ስልሳ አምስት) ቅጠል ቆርቆሮ የተሠራ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በአፈ ከሳሽ ወ/ሮ ፋንታዬ ወልደየስ እና በአፈ ተከሳሽ አቶ ደስታ ሸዋሲናድ መካከል ስላለው የአፈፃጸም ክስ ጉዳይ ግራ ቀኙ ባላቸው የመኖሪያ ቤትና ቦታ ላይ ለመስማማት ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት በሞላሌ 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ዞን 5 ውስጥ ቢስኮረብታ ከተባለው ስፍራ አዋሳኙ ከምስራቅ የበላይ ገብረሕይወት ቤትና ቦታ ከምዕራብ የለወግ በፋንታው ቤትና ቦታ ከሰሜን መንገድ ከደቡብ ወ/ሮ ብዙዬ ተሰማ ቤትና ቦታ መካከል የሚገኘው የቦታው ስፋት 200 ካሬ ሜትር የሆነ የመኖሪያ ቤት እና ቦታ 65 (ስልሳ አምስት) ቅጠል ቆርቆሮ የተሠራ መነሻ ዋጋው ብር 1,284,481.47 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አንድ ብር ከ47 ሳንቲም ) ይህንን የመኖሪያ ቤትና ቦታ ከመነሻው ዋጋው በላይ በግልፅ ጨረታ ስለሚሸጥ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ/ም ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ጨረታው ይካሄዳል፡፡ ጨረታው የሚካሄድበት ሰዓት ከጠዋቱ ከ4:00-6፡00 ሰዓት ተገኝተው መጫረት ይችላሉ፡፡ ይህንን ቤትና ቦታ በግልፅ ጨረታ መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በቦታው ተገኝቶ ተጫርቶ መግዛት ይችላል፡፡ የጨረታው አሸናፊ አካል የሆነ ያሸነፈበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ የሚያሲዝ ሲሆን ቀሪውን 3/4ኛውን ደግሞ በ15 ቀን ውስጥ አሟልቶ የሚያቀርብ መሆኑን አውቀው መጫረትና መግዛት የሚፈልጉ በቦታው ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ፍ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ፡-09-21-01-38-86 መደወል ይችላሉ
የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-08-30 12:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: North Shewa Zone Menz Mama Meder Woreda Court
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T08:29:13.000Z