Office and commercial space rental
ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕንፃ ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለልን ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡ ሕ/006/2018
ሕብረት ባንክ አ.ማ. አዲስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክ/ከተማ፣ በወረዳ 7 ሰንጋ ተራ አካባቢ አዲስ ባስገነባው የዋናው መስሪያ ቤት ሕንፃ ዘጠነኛ /9ኛ/ ወለልን ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም ኪራይ ፈላጊዎች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት የመጫረቻ ሰነድ ሊያቀርቡ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣ ከ2 ቀናት በኋላ ከሃምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ነሐሴ 05 ቀን 2018 ዓ.ም. የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በአቅራቢያ በሚገኙ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር IN0403007 በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን በልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7 ሰንጋ ተራ ወለል አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ወለል በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በመገኘት መግዛት ይቻላል።
- ለጨረታ የቀረበውን ወለል ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾችጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ማለትም ከሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ነሃሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ውስጥ ሰኞ፣ ዕሮብ እና አርብ ከጠዋቱ 3፡00 - 10፡00 ሰዓት በባንኩ ዋና መ/ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሞልተው ከማስገባታቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተካተተውን የተጫራቾች መመሪያ በደንብ ማየት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለጨረታ የቀረበውን ይዞታ ቢከራዩ የሚከፍሉትን የአንድ ወር ኪራይ አንድ አራተኛ (25%) በባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የጨረታሰነዱን ሲያቀርቡ ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የዋስትናው የአገልግሎት ጊዜውም Validity Date/ ዘጠና (90) ቀናት ይሆናል፣
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያስይዙትን የባንክ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) የሚያሰሩት ከሕብረት ባንክ ውጪ በሆኑ በማንኛውም ባንኮች መሆን አለበት።
- እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታው አስፈላጊ የሆኑ ሰነዶችን በማሟላት ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 7፣ ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ 19ኛ ፎቅ በግዥ እና ኮንትራት አስተዳደር መምሪያ በሚገኝ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ነሃሴ 1፣ 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ነሃሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አራተኛ /4ኛ/ ወለል ላይ በሚገኘው አዳራሽ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ያልቀረበ የመጫረቻ ሰነድ/ተጫራች ከውድድር ሊሰረዝ ይችላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011- 470 4172 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ!!
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ነሃሴ 1፣ 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ
- Bid opening: 2026-08-12 10:00
- Bid opening (note): ነሃሴ 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hibret Bank S.C.
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026), Reporter (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T08:52:10.000Z