Stationery and office consumables

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ሙጢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የቢሮ ቋሚ እቃዎች አና የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች፣ የኤሌትሮኒክስ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የመኪና እና የሞተር ሳይክሎች ጎማዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ሙጢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት አመት በስሩ ላሉት መንግስት ሴክተሮችና ቀበሌ መስተዳድሮች የሚያስፈልጉ ለቢሮ እቃዎች የሚውሉ፡-

  1.  የቢሮ ቋሚ እቃዎች አና የጽህፈት መሳሪያዎች
  2. የተለያዩ የቢሮ እቃዎች
  3. የኤሌትሮኒክስ እቃዎች
  4. የጽዳት እቃዎች
  5.  የደንብ ልብስ
  6. የመኪና እና የሞተር ሳይክሎች ጎማዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫረቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል

  1. በዘርፉ የተሰማሩበት ሥራ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ እንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. የግብር ከፋይነት ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% ቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ጨረታውን ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ ወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ የሚችል።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500 ( አምስት መቶ) ብር በመክፈል በጎሮ ሙጢ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
  6.  ጨረታው በማስታወቂያ ወይም በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፋታል ዕለቱ አመት በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
  7. በጨረታው ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO (ሲፒኦ) በቢሮ ሥም አሰርቶ ማቅረብ የሚችል።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ (አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

ሀ. የጨረታው አሸናፊ በተባለበት ቀን እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል

ለ. ተወዳዳሪ ዝርዝር ዋናውን በቀረበለት ሰነድ ላይ መሙላትና ስርዝ ድልዝ ካለበት ተቀባይነት የለውም

ሐ. ተወዳዳሪው የእቃውን ዝርዝር ሲያቀርብ የተመረተበትን አገር አይነት መጥቀስ አለበት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0905689856/0926712526/0948637463

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ሙጢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ ወይም በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-15 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ ወይም በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: East Hararghe Zone Goro Mutii Woreda Finance Office
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T09:09:05.000Z
← Back to all tenders