Stationery and office consumables
የኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Description
የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም
- ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አላቂ ዕቃዎች
- የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች /ፈርኒቸሮች/
- የደንብ ልብሶች የወንድና የሴት ጫማዎች
- ለፅዳት የሚውሉ ቁሳቁሶች
- የተለያዩ የመኪና ጎማዎች ወዘተ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ መግዛት ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማናቸውም ተጫራቾች
1. የሚፈለግበትን የመንግስት ግብርና ታክስ በህጉ መሰረት የከፈለና ፍቃዱን ያሳደሰ
2. የታክስ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለውና የሚያቀርብ የ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የ (VAT) ተመዝጋቢነት መረጃቸውን ማቅረብ አለባቸው።
3. በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ያልታገደ
4. በሚያቀርባቸው እቃ ጥራት የታወቀና ለዚህም ከታወቀ የመንግሥት መ/ቤት ማስረጃ የሚያቀርብ
5. የጨረታ ማስከበሪያ 5000 /አምስት ሺህ / የኢት ብር ማስያዝ ይኖርበታል።
6. ተጫራቾች የእቃውን ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉትን እቃ በራሳቸው ወጪ እስከ ወረዳው ንብረት ክፍል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች የሚጨረቱበትን እቃ የራሳቸው አርማና ማህተም ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በትክክል በመፃፍ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሳጥን እስከ 15ተኛው የሰራ ቀን እስከ 10፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
9. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1፣ 2፣ 3 እና 4 ላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒ በዋጋ ማቅረቢያ ኢንቨሎፕ ውስጥ በመክተት አብረው ማሸግና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል።
11. ቢሮው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-ስርዝ ድልዝ ያስው የማይነበብ የሚያደናግሩ ሰነድ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም::
አድራሻችን፡- ምስ/ሐረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0940590501 ጠይቀው ይረዱ
የኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-15
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-15 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: የኩርፋ ጨሌ ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት
- Bid bond: 5000 (አምስት ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T11:07:57.000Z