Property and building foreclosure

ድጋሚ የወጣ የቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ ባለመብት ወ/ሮ የሮምነሽ ተገኝ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ አሸናፊ ጉጃ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.85630 በ11/08/2014ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.88689 በቀን 21/11/2014ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.88689 በቀን 20/3/2015ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት

1ኛ. በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 450 ቁጥር 18/72/25/046/00 የተመገበ ተነጻጻሪ ካርታ ያለው ጠቅላላ የቦታ ስፋት 749ካ/ሜ ቤቱ ያረፈበት 344.72ካ/ሜ ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው 217.28 ካ/ሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደረሰው የቦታ ስፋት 562 ካ/ሜ ከጠቅላላው ይዞታ ላይ የመንገድ ጥናት 97 ካ/ሜ ይነካዋል ይዞታው LDP Relocaion site ለመልሶ ማስፈሪያ የተያዘ ነው የሐራጅ መነሻ 14,011,646 (አስራ አራት ሚሊዮን አስራ አንድ ሺህ ስድስት መቶ አርባ ስድስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ ም በሐራጅ ለመሽጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.88689 በቀን 8/11/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 3,502,911.50 ( ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ አንድ ከ50/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

2ኛ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 451 ካርታ ያለው ተነጻጻሪ ካርታ ያለው ጠቅላላ የቦታ ስፋት 538ካ/ሜ ቤቱ ነገር ግን በቀን 10/07/2004 ወጪ የሆነው ካርታ በፕሮፖርሽን ያደረገው በመሆኑ ቤቱ ከተቅላላው በፕሮፖርሽን የሚደርሰው 187ካ/ሜ ከጠቅላላው ይዞታ ከቤት ቁጥር 450 እና 451 ላይ የመንገድ ጥናት 97 ካ/ሜ ይነካዋል ይዞታው LDP Relocaion site ለመልሶ ማስፈሪያ የተያዘ ነው የሐራጅ መነሻ 7,015,371 (ሰባት ሚሊዮን አስራ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ አንድ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.88689 በቀን 8/11/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 1,753,842.75 ( አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሁለት ከ75/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤጽ/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑንእንገልጻለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-02 12:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T11:14:44.000Z
← Back to all tenders