Property and building foreclosure
የቦታው ስፋት 219 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አየሉ ደምሴ እና የፍ/ባለዕዳ ሀይሉ ጎንፋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/121731 በ12/03/2108 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/123822 በ8/4/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 04 በይዞታ መለያ ቁጥር AA000070407526 የሆነ በአየሉ ደምሴ ሄይ እና ኃይሉ ጎንፋ ጉርሙ ስም የተመዘገበ በሰሜን ዲባባ ጉርሜሳ በደቡብ መንገድ በምስራቅ ቄስ ፍስሀ ከበደ እና በምዕራብ ቢላል ያሲን የሚገኙ አጎራባቾች ሲሆኑ የቦታ ስፋት 219 ካ/ሜ የቤቱ ስፋት 96.58 ካ/ሜ ለይዞታው ተደራሽ የሚሆን የ25 ካ.ሜ ስፋት ያለው መንገድ ለይዞታው ተደራሽ ሲሆን የተጠቀሰው መንገድ የተያዘውን 7.25 ካ.ሜ ይነከዋል በተጠቀሰው መንገድ የሚከናወን አዲስ ግንባት በተመለከተ ከተጠቀሰው መንገድ አቅጣጫ በኩል 3 ሜትር ሴት ባክ መጠበቅ አለበት እንዲሁም ከሌላ ባክ ቀሪ 500 ካ.ሜ እና 20 ሜትር የይዞታ የፊት ገጽ መሆን ይኖርበታል። የሆነ ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 7,377,906 (ሰባት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስድስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.123822 በቀን 9/11/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 1,844,476.50 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አራት ሺህ አራት መቶ ሰባ ስድስት ከ50/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር+251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-08-31 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T11:22:57.000Z