Disposal, scrap and surplus sales

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 01/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሀራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ በመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

በሀራጅ ጨረታ ቁጥር 01/2018 በ 29/11/2018 የተለያዩ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ጫማዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ የሞባይል ግላሶችእና ከቨሮች፣ የእጅ ሰዓቶች፣ ስፔርፓርቶች፣ የእይታ ዕቃዎች መነፅሮች፣ መሬት ምንጣፍ፣ ኮስሞትክስ እና መዋቢያዎች፣ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የእጅ ሰዓቶች፣ የእስፖርት መስሪያ መሳሪያዎች፣ ኳስ፣ የተለያዩ አርተፍሻል ጌጣጌጥ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1. የተደሰ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል።

2. በጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድረዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።

3. በሀረጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ሙድአነኖ ቢሮ በመቀረብ ብር 100 በመክፈል ሰነድ ለመግዛት ዘወትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰአት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቀረብ ማየት ይቻላል። ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ነው።

5. ለሀራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾቸ የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።

6. ተጫራች በሀራጅ ጨረታ በመጫረት በኮዱ የተቀመጠ ብር ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድረዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

7. በሀራጅ ጨረታ ለወጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች በጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ለኮዱ የተቀመጠ ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

8. የሀራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በእለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ጨረታው ይጀምራል።

9. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሽናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

10. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።

11. ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለሰፀው ቀናቶች ውስጥ ከፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።

12. የጉምሩክ ኮምሽንቅ/ጽ/ቤቱጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 ( 09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል

የጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-05 10:00
  • Region: Dire Dawa
  • Publishing entity: Ministry of Customs Diredawa Branch Bureau
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T11:38:19.000Z
← Back to all tenders