Oromia

መቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ አም/ኅ/ሥ/ ዩኒየን ንብረትነቱ የራሱ የሆነ ያገለገለና የሚሠራ ሲኖ ትራክ መኪና ጋቢናውንና ተሳቢውን የነዳጅ ታንከር ቦቴ (ሎቤድ) በአንድ ላይ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ በመነሻ ዋጋ ከቫት በፊት በ10,000,000.00 (አሥር ሚሊዮን) ብር አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የመኪና ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

መቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ አም/ኅ/ሥ/ ዩኒየን ንብረትነቱ የራሱ የሆነ ያገለገለና የሚሠራ ሲኖ ትራክ መኪና ጋቢናውንና ተሳቢውን የነዳጅ ታንከር ቦቴ (ሎቤድ) በአንድ ላይ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ በመነሻ ዋጋ ከቫት በፊት በ10,000,000.00 (አሥር ሚሊዮን) ብር አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1-የመኪናው ሰሌዳ ቁጥር (profile)

  • የጋቢናው ሰሌዳ ቁጥር ET-3-43263 ሞዴል ZZ425753241V የተሰረበት ሀገር ቻይና የተሰራበት ዘመን 2009 G.C የሻንሲ ቁጥር LZZ5CL51329A429807 የሞተር ቁጥር 091107021647

2-የተሳቢው ወይም የቦቴ ሰሌዳ ቁጥር

  • የተሳቢ ሰሌዳ ቁጥር ET-3-14302 ሞዴል MIE/36H/fTL/3/12.5 የተሰረበት ሀገር ኢትዮጵያ መስፍን ኢንጂነሪንግ የተሰራበት ዘመን 2009 G.C የሻንሲ ቁጥር CTS-496-09 ቦቴ የመጫን አቅም 50,000 ሌትር መሆኑን እየገለፅን፡-

ተጫራቶች ማሟላት ያላበቸው ዋና ዋና መስፈርቶች

1.ማንኛውም ተጫራች የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ወይም የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት ወይም ኅ/ሥ/ ማህበራት ከሆኑ በአወጁ መሰረት የተቋቋመበት ሰርትፍኬት ማቅረብ አላበቸው።

2. የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ወይም TIN NUMBER ያለቸው መሆን አለባቸው።

3. ከመንግስት ግብር (ዕዳ) ነፃ መሆኑን መረጋጋጫ ሰርትፍኬት ማቅረብ የምችል መሆን አለበት።

4. ተጫራቾች የጨረታውን የቴክኒካልና የፋይናንሻል ሰነድ ለያብቻ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያያ በሰም በተሸጋ ፖስታ የድርጅቱ ክብ ማህታም ያረፋበት አዘገጅቶ መቅረብ አለበት።

5. የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ዋጋ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር ማስያዝ አለበት።

6. የጨረታው ሰነድ የምሸጠው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ16 (አሥራ ስድስት ቀን) ታከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት 2፡30-11፡30 ተሸጦ የጨረታው ቀነ ገደብ ካለቀ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች የቴክንክና የፋይናንሻል ሰነዳቸውን ኦርጅናልና ኮፒ በተለያያ ፖስታ ተሸጎ ለዚሁ ዓለማ በተዘገጀው የጨረታ ሳጥን ገብቶ ሳጥኑ ይታሸግና በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካይ እና ተዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል። የቴክኒክ ሰነዱ በቅድሚያ ይታይና ቴክንኩን ያላለፈ ወገን የፋይናንሻል ሰናዳቸውን ሳይታይ ከጨረታ ውጪ ሆኖ ሰናዳቸው ተመላሽ ይሆናል። ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ከላው ተቀባይነት አይኖረውም።

7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ ጥያቄ፣ አስታያየት፤ ማስተካካያ ካለው የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ 5 ቀን በፍት ብቻ ለድርጅቱ በፁሁፍ ማቅረብ አለበት። በዚሁ አግባብ ድርጅቱም ተመሳሳይ ጥያቄ ካላው የጨረታ ሰነዱ ከመከፈቱ 5 በፍት ለተጨረቶች ማወቅ አለበት። የጨረታ ሰነድ ቋንቋ የሚቀርበዉ በአማርኛ ይሆናል።

8. የጨረታ ማስከበሪያ CPO በዩኒየኑ ሙሉ ስም 500,000.00 (አምሥት መቶ ሺህ ብር) በዩኒየኑ ሙሉ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሒሳብ ቁጥር 1000041208434/ በኦሮሚያ ሕ/ሥራ ባንክ በሒሳብ ቁጥር 1000006718586 እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያና ዳንብ መሰረት በተቋቋመ ማንኛውም ባንክ ማስያዝ ይችላሉ።

9 -መኪናውን በተመለከተ ውዝፍ የመንግሥት ግብር በዩኒየኑ ወጪ የሚሸፈን ሆኖ የሥም ማዛዋሪያ ክፍያ ተጨረቹ የምሸፍን ይሆናል።

10- ማንኛውም ተጫራች ሁለቱን መኪና ነጠጥሎ መጨረትና መግዘት አይቻልም። እንዲሁም ማንኛውም ተጫራች ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታውን አስገዳጅ ህግ የማይወጣ ከሆነ በአወጅ ቁጥር 218/2011 እና በሕብረት ሥራ ማህበራት ግዥ መማሪያ ቁጥር ደ/ገ/007/2017 መሰረት ድርጅቱ አስፈላጊውን እርምጃ የምወስድ መሆኑን ያሳውቃል።

11 የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ከታወቀ መኪናውን ሙሉ ክፍያውን በአንድ ጊዜ ክፍያውን በዩኒየኑ ከላይ በተጠቀሰው ሒሳብ ቁጥር በማስገባት መኪናውን እስከ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ አጠናቆ ማንሳት አለበት። ከተወሰነው ቀን ከላፋ ተጫራቹ ለዩኒየኑ ቅጣት በየቀኑ 2,000.00 (ሁለት ሺህ) ብር ለመክፈል በህግ ፍት የምፃናና የሚገዳድ ይሆናል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ከገኛ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል የመሰረዝ መብቱ በህግ ፊት የተጠበቀ ነው።

የጨረታ ማስረከቢያ አድረሻ:- በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምሥራቅ ሸዋ ዞን፤ ዱግዳ ወረዳ፤ መቂ ከተማ፡- መቂ ባቱ አትክልትና ፍራፍሬ አም/ኅ/ሥ/ ዩኒየን (ቢሮ ቁጥር-2) ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022 118 1402/ 09 09 34-34-34/ 09-10-92-95-36/ 09-20-36-80-41 መደወል ይቻላል።

መቂ ባቱ አትክልትና አምራቾች /ኅ/ሥራ ዩኒየን ኃ.የተወሰነ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-15
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ16 (አሥራ ስድስት ቀን) ታከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት 2፡30-11፡30 ተሸጦ የጨረታው ቀነ ገደብ ካለቀ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-15 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ16 (አሥራ ስድስት ቀን) ታከታታይ የሥራ ቀናት ጠዋት 2፡30-11፡30 ተሸጦ የጨረታው ቀነ ገደብ ካለቀ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Meki Batu Horticultural producers Union
  • Bid bond: 500,000.00 (አምሥት መቶ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
  • Posted at: 2026-07-30T08:27:53.000Z
← Back to all tenders