Stationery and office consumables
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ጉጂ ዞን የሀምበላ ዋመና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት በወረዳ ስር ለሚገኙ የመስሪያ ቤቶች ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ እስቴሽነሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማ ከአቅራቢ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ጉጂ ዞን የሀምበላ ዋመና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት በወረዳ ስር ለሚገኙ የመስሪያ ቤቶች ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ እስቴሽነሪ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማ ከአቅራቢ ድርጅት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
አስፈላጊ መስፈርቶች
1. ተጫራቾች በየንግድ መስኩ ሕጋዊ የሆነ ንግድ ፈቃዳቸውን ዓመታዊ የስራ ግብር የከፈሉበትን በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክሲ (VAT) የተመዘገቡበትን የሚገልጽ መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለእያንዳንዱ ጨረታ ዓይነት 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታው ኦሪጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፒ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒ እና ኦሪጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት
5. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ በመንግስት የግዢ መምሪያ መሰረት ይበረታታሉ።
6. ጨረታው የሚከፍተው ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው በሥራ ሰዓት ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤተ ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በጽሑፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ6ቀን ውስጥ የጨረታ ውል ማስከበሪያ የሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 30% በባንክ በተመሰከረ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከመስሪያቤቱ ጋር መፈራረም አለበት።
8. አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
9. ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መስሪያ ቤቱ ግምጃቤት ማምጣት እና በራሱ ወጪ መገጣጠም የሚችል።
10. መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 12 70 10 62/ 09 16 38 46 70
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ጉጂ ዞን
የሀምበላ ዋመና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 13:30
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው በሥራ ሰዓት ከቀኑ 7፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-17 14:30
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው በሥራ ሰዓት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Hambela Wamena Woreda F/E/D/Bureau
- Bid bond: 30,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
- Posted at: 2026-07-30T08:57:04.000Z