Office furniture

በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያየ መደበኛ ጨረታ ለ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2019 ዓ.ም

በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያየ መደበኛ ጨረታ ለ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡- ፅህፈት መሳሪያ
  • ሎት 2፡- የደንብ ልብስ
  • ሎት 3፡- የመኪና እቃ
  • ሎት 4፡- ዘር እና ግብርና ግብአት
  • ሎት 5፡- የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት 6፦ የተለያዩ የአዳርሽ እና የካፌ ፈርኒቸር
  • ሎት 7፦ የመኪና ጥገና

1. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው እቃ ወይም አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልጽ ለይተው መጻፍ አለባቸው።

3. ተጫራቾች በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድረ ገጽ (ዌብ ሳይት) ላይ በዘርፉ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ላይ ወይም አገልግሎቶች ሳምፕል ወይም ናሙና ለመስራቤቱ በማቅረብ የጥራትና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመገማሉ።

6. ተጫሪ ቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን በመሰረዝ በመደለዝ ማሻሻያ ማድረግና መለወጥ አይችሉም።

7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ ተጫራቾች ካደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያከተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ለሎት 1፡- 25,000 ፤ ለሎት 2፡-25,000፧ ለሎት 3፡- 25,000፣ለሎት 4፡- 25,000፣ ለሎት 5፡- 25,000 ሎት 6፡ 100,000 ሎት 7. 30,000 በ ኢትዬጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።

10. የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኢንቨሎፕ ታሽገው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ፊርማቸውንና ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል በስራ ስዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 የጉ/ክ/ከ/አ የዲዛይን ና ግንባታ ስራዎች ፑል/የአስ/ፋይ/ፅ/ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

12. የካፒታል መጠናቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ የሆኑ ተጫራቾች ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

13. የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው የስራ ቀን ከሆነ በ10 ተከታታይ ቀናቶች በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆንን እየገለፅን ጨረታው አየር ላይ በዋለ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4:30 በጉ/ክ/ከ/የዲ/ግ/ስ/ፑል/የአስ/ፋይ/ዕ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

15. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናሉ።

16. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

17. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ባይሆን ከጨረታ ይሰረዛሉ።

18. ተጫራቾች በንግድ ፈቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡የተጫራቾች ማህተም እና የንግድ ፍቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል። 

19. በጨረታ መወዳደሪያ የሚያቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።

20. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ይህ ግን በጨረታ የስያዙት /ሲፒኦ/ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።

21. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የእቃ ብዛት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ከአሸነፈው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

22. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን በመሰረት ናሙና ውይም ሳምፕል ማስገባት ይኖርበታል።

ማሣሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገም ጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን ና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 011_8 12 10 96

በጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት 


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-11 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው አየር ላይ በዋለ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Design and Construction Works Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
  • Posted at: 2026-07-30T09:24:42.000Z
← Back to all tenders