Property and building foreclosure
የመኖሪያ ቤቶች ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ኑሩያ አሕመድ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ኑረዲን ናስር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 139232 በ13/10/2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ 150457 በ14/11/2017ዓ.ም በኮ/መ/ቁ 150457 በ5/03/2018ዓ.ም በኮ/መ/ቁ 150457 በ28/09/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት
1ኛ በወ/ሪት ኢክራም ኑረዲን ስም የተመዘገበ በኮ/ቀ/ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የሚገኝ መኖሪያ ቤት የይዞታ ስፋት 225 ካ/ሜ በከፊል 105 ካ/ሜ Green Area የሚነካው ሆኖ ሰነድ አልባ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,569,910 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አስር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
2ኛ በኦሮሚያ ክልል ሽገር ሲቲ ከተማ ኮዬ ፈጬ የሚገኝ በተጠሪ ስም የተመዘገበ ባለ አንድ መኝታ ቤት የቤቱ ስፋት 59.45ካ/ሜ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕዳ አለበት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,039,439.26 ( አንድ ሚሊዮን ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ከ26/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትጵዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት C.RO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሽጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-08-31 14:30
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
- Posted at: 2026-07-31T07:27:13.000Z