Stationery and office consumables

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሶዶ ዳጪ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተሮች በ2019 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮችን እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዘት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2019

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሶዶ ዳጪ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተሮች በ2019 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ፤ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮችን እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዘት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ አቅራቢ መወዳደር ይችላል።

የቀረቡት መስፈረቶች፡-

1. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ወይም ያልከፈሉበትን ምክንያት ከገቢዎች ጽ/ቤት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።

2. በገ/ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ፤ የቲን (TIN) የቫት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለበት።

4. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች በኢት.ደ.ኤጀ. የተረጋገጠ መሆን አለበት

5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ ሰነድ ላይ የመንግስት ታክስ አካቶ (ደምሮ) መስራት ይኖርበተል ነገር ግን ሳይደምር ቢያስገባ እንደ ደመረበት ታስቦ ይሰራል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሙሉውን በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) መግዛት ይችላል።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ወይም 24/11/18 እስከ 14/12/18 ድረስ ከሶዶ ዳጪ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በተከታታይ የሥራ ቀናት ከግዥ ከፍል ገዝተው በ15ኛ የስራ ቀን እስከ 11፡20 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ 7 ቁጥር ላይ በተጠሰው አድራሻ ለሰነዱ በተዘገጀ ሳጥን ማስገባት ይችላል።

9. ጨረታው ማ/ያው ከወጣበት በ15ኛው በሥራ ቀን ከቀኑ 11፡21 ሰዓት ተዘግቶ በ16ኛው በሥራ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አዳራሽ በይፋ ይከፈታል።

10. ከተገለጸው የጨረታ ግዜ ሰሌዳ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ ለሚመጡ ተጫራቾች መስሪያ ቤቱ የማይቀበል መሆኑን ይገልጸል።

11. ጨረታውን የሚያሸንፉ ተጫረቾች ሁሉ ያሸነፉትን ዕቃ በሙሉ እስከ መ/ቤቱ ዕቃ ግምጃቤት ድረስ በራሱ ወጭ ማድረስ የሚችል

12. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡-

ተጫራቾች አስፈላጊውን ናሙና የደንብ ልብስ፣ እስክርቢቶ፤ አጀንዳ የኮምፒውተር ወረቀትና ማስተወሻ ደብተሮችን ጽ/ቤቱ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡-

በደ/ም ሸዋ ዞን የሶዶ ዳጪ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በቡታጅራ መንገድ ከአ/አ 74 ኪ.ሜ

በስልክ ቁጥር 0113 631 733 / 0911 693 710 / 0920 016 709

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የሶዶ ዳጪ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-17
  • Bid closing time: 17:21
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው በሥራ ቀን ከቀኑ 11፡21 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-18 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው በሥራ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: South West Shewa Zone Sodo Dachi Woreda F/E/D/Bureau
  • Buyer address: በቡታጅራ መንገድ ከአ/አ 74 ኪ.ሜ
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
  • Posted at: 2026-07-31T07:41:53.000Z
← Back to all tenders