Stationery and office consumables

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና ዓላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ዞን ፋይናስና ፕላን መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና ዓላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ ሎት2. የጽዳት ዕቃዎች ሎት3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ሎት 4. ሞተር ሳይክል ሎት 5. ከውጭ ሃገር የሚገቡ ፈርኒቸር ሎት 6. በአከባቢ ማቴሪያል ሆኖ በዘመናዊ ማሽን የሚሰሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ፈርኒቸር ሎት 7. በአከባቢ ማቴሪያል የሚሰራ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣

  • በዘመኑ የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ማቀረብ የሚችል፣
  • የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  • የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ያለው፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤

ከላይ በዝርዝር የተቀመጠዉን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ፤

    • ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
    • ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
    • ሎት 3. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
    • ሎት 4. ሞተር ሳይክል ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
    • ሎት 5. ከውጭ ሃገር የሚገቡ ፈርኒቸር ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/
    • ሎት 6. በአከባቢ ማቴሪያል ሆኖ በዘመናዊ ማሽን የሚሰሩ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ፈርኒቸር ብር 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/
    • ሎት 7 በአከባቢ ማቴሪያል የሚሰራ ፈርኒቸር ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ እና በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አይቻልም።
  • ተጫራቾች ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሽጉ በኃላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
  • ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ/ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በህጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት፤
  • በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት ፤
  • ጨረታዉ የሚከፈተዉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኃላ በ22ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።
  • የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ነው።
  • ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃዎች ጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን በኃላ ለ3 ወር ማለትም ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቃያል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 131 0108 መደወል ይችላሉ።

በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ዋና ሥራ ሂደት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-21 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
  • Posted at: 2026-07-31T08:14:12.000Z
← Back to all tenders